በ19ኛው ምዕት ዓመት በአፄ ዮሐንስ 4ኛና በተከታያቸው በአፄ ምኒልክ 2ኛ ዘመን የጎጃም ንጉሥ የነበሩት ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ያረፉበት 122ኛ ዓመት መታሰቢያ በመናገሻ ከተማቸው በደብረ ማርቆስ ከተማ ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ታስቧል። ዝክራቸው በተለይ በከተማዋ በሚገኘው በመልዕልተ አድባር ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በያሬዳዊ ዜማ ከመከበሩ ባሻገር የንጉሡ የተለያዩ ንዋዮችም ለዕይታ ቀርበዋል፡፡ በአፄ ዮሐንስ አማካይነት ጥር 12 ቀን 1873 ዓ.ም. በጎጃም ከመንገሣቸው በፊት ‹‹ራስ አዳል ተሰማ›› ይባሉ የነበሩት ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ያረፉት ጥር 2 ቀን 1893 ዓ.ም. ነበር፡፡ ፎቶዎቹ በዕለተ ዝክሩ የነበረውን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡