የሰው ክብሩና መመዘኛው ‹‹እኔ እንደዚህ ነኝ!››፣ ‹‹እንዲህና እንደዚህ ዓይነት ሀብት አለኝ›› የሚለው ባዶ ክብር አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት የውሸት ተግባራት ከመከበር ይልቅ ውርደትን ያመጣሉ፡፡
በውሸት ራሳችንን ከፍ ስናደርግ ባዶነታችንን ማሳየታችን እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ አበው ‹‹ባዶ ዕቃ ብዙ ድምፅ ያሰማል!›› ይላሉ፡፡ ባዶ የሆነ ሰው ስለራሱ ብዙ ጉራዎችን መንዛቱ መታወቂያው ነው፡፡ ስለራሳችን ጉራ ስንነዛ ግን ባዶነታችንን ትልቅ ማድረጋችን እንደሆነ እናስተውል፡፡ ፊኛ ትልቅ ቢመስልም በመርፌ ነካ ሲደረግ ግን ውስጡ ባዶ ነው፡፡ ሀሰተኛ ሰውም እንደፊኛ ራሱን ከፍ ቢያደርግም አንድ ቀን በእውነት መርፌ ሲነካ ባዶ መሆኑ ይገለጥበታል፡፡
- ዳንኤል ዓለሙ ‹‹ራስን የመለወጥ ምሥጢር›› (2005)