Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሚዲያን የሚያበረታቱ ሕጎች ቢኖሩም ተግባራዊ እየተደረጉ አለመሆኑ ተገለጸ

ሚዲያን የሚያበረታቱ ሕጎች ቢኖሩም ተግባራዊ እየተደረጉ አለመሆኑ ተገለጸ

ቀን:

  • ካፒታል ጋዜጣ 25ኛ ዓመት (ሩብ ምዕተ ዓመት) በዓሉን አከበረ

በኢዮብ ትኩዬ

በኢትዮጵያ ሚዲያን የሚያበረታቱ ሕጎች ቢኖሩም፣ ተግባራዊነታቸው ላይ ግን ችግር እንዳለ ምሁራንና የሚዲያ አካላት ተናገሩ፡፡ ምሁራንና የሚዲያ አካላት ይህን የተናገሩት ካፒታል ጋዜጣ የ25ኛ ዓመት (ሩብ ምዕተ ዓመት) በዓሉን ባከበረበት ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ነው፡፡  

በኢትዮጵያ ያለው የሚዲያ ሁኔታ አሉታዊና አዎንታዊም ተፅዕኖ እየገጠመው መሆኑ በመርሐ ግብሩ ላይ ተነግሯል፡፡

የገጠሙትን አሉታዊና አዎንታዊ ተፅዕኖዎች በመቋቋም ላለፉት 25 ዓመታት (ሩብ ምዕተ ዓመት) በኅትመት ላይ የሚገኘው ካፒታል እንግሊዝኛ ጋዜጣ (Capital  Newspaper)፣ የጋዜጠኝነትን መርሆዎችን በመከተል ከመሥራቱም፣ በተጨማሪ ለአገርም ያደረገው አስተዋጽኦ ቀላል የማይባል መሆኑን በመጠቆም፣ ያሉትም ሆኑ አዳዲስ ወደ ዘርፉ የሚገቡ ሚዲያዎች ጠንክረው መሥራት እንዲችሉ መንግሥት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት፣ የጋዜጣው ማኔጂንግ ኤዲተር ትዕግሥት ይልማ ተናግረዋል፡፡

ካፒታል ጋዜጣ በዋነኛነት የቢዝነስና ኢኮኖሚክ ዘገባዎችን የሚዘግብና የሚተነትን ጋዜጣ ከመሆኑ አንፃር፣ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ መከፈት፣ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል ጫፍ መድረስ፣ የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፍቀድና የቴሌኮም ተቋማት መምጣት ሲታሰብ፣ ያለ ጠንካራ ሚዲያ አስቸጋሪ ስለሚሆን፣ የሚዲያውን ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ ማሳደግና ማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራበት የሚገባ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ማኔጂንግ ኤዲተሯ ጋዜጣው በ25 ዓመታት ውስጥ ስላበረከተው አስተዋጽኦና ስላሳለፋቸው ተግዳሮች አውስተው፣ አሁን አሁን ዲጂታል ሚዲያው በመደበኛ በተለይም የኅትመት ሚዲያው ላይ እየፈጠረበት ያለውን ተፅዕኖ ተሻግሮ፣ እንዴት መቀጠል እንዳለበት የሚመክር የፓናል ውይይት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 29 ሐሳብን የመግለጽ መብት መፈቀዱና ዲጂታል ሚዲያ ሕጋዊ ሆኖ መመዝገቡ መልካም ቢሆንም፣ የሕጉ ጉዳይ በተግባር ሲታይ ግን ብዙ ጉድለቶች እንዳሉበት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ ተናግረዋል፡፡

‹‹ያለገደብ ሐሳብን የመግለጽ መብት አለ፣ መረጃም የማግኘት መብት አለ ይባላል፤›› ያሉት ሰብሳቢው፣ ‹‹መረጃ ለማግኘት ግን አስቸጋሪ እየሆነ ነው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አክለውም፣ ‹‹አንዳንድ የግል ሚዲያዎች መረጃ ለማግኘት ሲቸገሩ፣ ሌሎች ደግሞ በቀላሉ ያገኛሉ፡፡ ይህ ደግሞ ዋነኛው ሚዲያ የሚያጋጥመው ተግዳሮት ነው፤›› ብለዋል፡፡

ሚዲያው ሥራውን ሲያከናውን ችግር እንዳያጋጥመው ከለላ ይደረጋል ቢባልም፣ በተግባር ግን ከለላ ሲደረግ እንደማይታይ አቶ አማረ ገልጸዋል፡፡

እንኳን የሚዲያ ከለላ ሊደረግ ጋዜጠኞች ምን አጥፍተው እንደሚታሠሩ፣ የት እንደታሠሩ የሚታወቅበት ሁኔታ አለመኖሩ ለሚዲያ አስቸጋሪ ስለመሆኑም ተወስቷል፡፡

እንኳን እንግሊዝኛ አማርኛ ጋዜጣ ማሳተም ከባድና አስቸጋሪ በሆነበት ሁኔታ፣ በክራውን አሳታሚ ድርጅት በየሳምንቱ እሑድ እየታተመ ሩብ ምዕተ ዓመት የቆየው ካፒታል ጋዜጣ፣ በአሳታሚዎቹና በሠራተኞቹ ብርቱ ጥንካሬና የሙያ ፍቅር እንጂ፣ ተግዳሮቶቹ እጅግ ብዙ መሆናቸው በባለሙያዎቹ ተወስቷል፡፡

ስም ማጥፋት ወንጀል ሳይሆን ፍትሐ ብሔር ነው ተብሎ አዋጁ ተሻሽሎ እያለ፣ በተግባር ሲታይ ግን ጋዜጠኛ ሲታሰር በወንጀል ወይም በፍትሐ ብሔር መሆኑ የማይታወቅበት አጋጣሚ ቢኖርም፣ ያንን ሁሉ ተቋቁሞ 25 ዓመታት በኅትመት መቆየት የሚደነቅና የሚበረታታ መሆኑም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...