Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልኪነ ሕንፃና ‹‹ከቤት እስከ ከተማ››

ኪነ ሕንፃና ‹‹ከቤት እስከ ከተማ››

ቀን:

በአበበ ፍቅር

በኢትዮጵያ የከተሞች ታሪክ ሲነሳ ቀዳሚዋ አክሱም ናት፡፡ ሥርወ መንግሥቱ ከአክሱም በኋላ የቀጠለባት ላሊበላ፣ ከዚያም ጎንደርና ሐረር በተለያዩ ዓረፍተ ዘመኖች በከተማነት ይታወቃሉ፡፡ በየከተሞቹ የነበሩት ሕንፃዎች የየራሳቸው አሻራ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ያኔ የነበረው የኪነ ሕንፃ (አርክቴክቸር) ሙያ አሁን ላይ በከተሞች ከሚገነቡ ሕንፃዎች ጋር የሚያገናኘው መስመር እንደሌለ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች ውስጥ የሚገነቡ ሕንፃዎች የዜጎችን ደኅንነት ከመጠበቅ ጀምሮ የአገርን ባህል፣ ማንነትና የአየር ንብረትን ያገናዘቡ መሆን አለባቸው ያሉት አርክቴክት ማኅደር ገብረመድኅን ናቸው፡፡

አርክቴክቸርና ምሕንድስና የአንድን አገር ሥልጣኔ፣ የከተሞቿን ዕድገት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ያሉት፣ የም አርክቴክቸር የተባለ አማካሪ ድርጅት ፕሪንሲፓል አርክቴክ የሆኑት ማኅደር ገብረመድኅን በኢትዮጵያ ዘመናዊ የአርክቴክቸር ትምህርት መስጠት የተጀመረው በ1959 ዓ.ም. ነው ይላሉ፡፡

አርክቴክት ማኅደር፣ በአፍሪካ ከተሞች በፍጥነት በማደግ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያም ይህንን ፈጣን ዕድገት ተቀላቅላ ያማሩና ዘመናዊ ከተሞችን በማስፋፋት ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡ አያይዘውም አማካሪ ድርጅቶችና ፖሊሲ አውጪዎች እንዲሁም በዘርፉ ባለሙያዎች በትክክለኛ ዳታ ላይ ተመርኩዘው ጥናቶችና የመፍትሔ ሐሳቦች ካቀረቡና ወደ ትግበራ ከገቡ ከተሜነት በርካታ ችግሮችን ለመፍታት አስተዋጽኦው የጎላ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

በትክክለኛ ፕላን ያልተመራ ከተሜነት ብዙ ችግሮችን ያስከትላል፡፡ ስለዚህ በከተሞች አመሠራረትና ዕድገት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠውም ይገባል ሲሉ አክለዋል፡፡

ለትምህርት፣ ለጉብኝትና ለተለያዩ ጉዳዮች በሚዘዋወሩበት ወቅት የተለያዩ የዓለም ከተሞች የደረሱበትን ዕድገት ከኢትዮጵያ ከተሞች ዕድገት ጋር በንፅፅር ለማኅበረሰቡ ለማሳየት፣ እንዲሁም ለሙያው አዲስ የሆኑትን ከቀደምቶቹ ጋር እየተገናኙ የሐሳብና የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበትን የሬዲዮ መድረክ ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹ከቤት እስከ ከተማ›› የሚል ድርጅት በማቋቋም ከዋና ሥራቸው በተጓዳኝ በሸገር ኤፍኤም 102.1 ላይ በዘርፉ ለ15 ዓመታት የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ለኅብረተሰቡ በተለይም በሙያው ላይ ለሚሳተፉ ሁሉ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ይወሳል፡፡

በዘርፉ ለአገራቸው በሙያቸውና ከሙያቸው ውጪ ብዙ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለ ሙያዎች በማኅበረሰቡ፣ በመንግሥትና በሙያ አጋሮቻቸው በቂ ዕውቅና ሳይሰጣቸው፣ በተለይ በሕይወት ሳሉ ሳይከበሩና ሳይወደሱ ማለፋቸው ከቤት እስከ ከተማን ለመመሥረት ያበቃቸው አንዱ ምክንያት መሆኑን አርክቴክት ማኅደር ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

 ‹‹አገር በአራሽ በቀዳሽ ትቀናለች›› የሚል ብሂል ቢኖርም፣ ነቃሽ የሌለው አገር በፅኑ መሠረት ላይ አይቆምም፣ ፈተናዎችም ይበዙበታል፡፡ ለዚህም መረጃ ከመስጠት፣ ከማስተማር አልፎ ብዙ ቀያሽ የሆኑትን ለማመሥገን የሚያስችሉ መድረኮችን በመፍጠር በተለያየ ትውልድ የሚገኙ አርክቴክቶችና መሐንዲሶችን በአንድ መድረክ በአካል ማገናኘት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

 ይህንን ያሉት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የከቤት እስከ ከተማን 15ኛ ዓመትና የከተማ ማዕከል አምስተኛ ዓመትን በማስመልከት በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ነበር፡፡

በመድረኩ ላይ ‹‹የአሰፋ በቀለ የሃምሳ ዓመት የአርክቴክቸር ጉዞ›› በሚል ከዛሬ አራት ዓመት ተኩል ገደማ የተደረገ ቃለ ምልልስ በዶክመንታሪ መልክ ቀርቧል፡፡

 በዝግጅቱ የአቶ አሰፋ በቀለ (1934-2010) ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ የሙያ አጋሮችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

 አቶ አሰፋ በቀለ ከማኅደር ገብረመድኅን ጋር በነበራቸው ቆይታ በሕይወት በነበሩበት ወቅት በሙያቸው ለአገራቸው በርካታ ሥራዎችን ሠርተው አስረክበዋል፡፡

 አቶ አሰፋ በቀለ ከተሳተፉባቸው ተቋማት መካከል ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት እንዲሁም የላሊበላ፣ የአክሱም፣ የአርባ ምንጭና የአሥመራ ዓለም አቀፍ ኤርፖርቶች ኪነ ሕንፃን በመሥራት ተሳተፈዋል፡፡

 ከእነዚህ በተጨማሪ የፌዴራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ፣ እንዲሁም በናይጄሪያ አቡጃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጨምሮ ከ33 በላይ ትልልቅ ተቋማት ላይ አሻራቸውን ያስቀመጡ የሙያ አባት እንደነበሩ በመድረኩ ተነግሯል፡፡

በቃለ ምልልሳቸው ወቅት አንዳንድ የከተማ መኖሪያ ቤቶች፣ መሥሪያ ቤቶችና ሆስፒታሎች ግንባታቸው የአገርን ገጽታ ያላገናዘቡ በቀጥታ ከውጭው ዓለም የተገለበጡ እንደሆኑ በመጥቀስ፣ ይህም በሙያው ላይ የሚሰጠው ትምህርት አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...