Monday, February 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኢትዮጵያዊው አማኑኤል ኢያሱ የመረብ ኳስ ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሆኑ

ኢትዮጵያዊው አማኑኤል ኢያሱ የመረብ ኳስ ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሆኑ

ቀን:

ዓለም አቀፉ የቮሊቦል (መረብ ኳስ) ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያዊው የመረብ ኳስ አሠልጣኝ አማኑኤል ኢሳያስ ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተርነት ደረጃ መስጠቱን ይፋ አድርጓል፡፡

አማኑኤል ኢሳያስ ሁለተኛው የኢንስተራክተርነት ደረጃን ያገኙ ኢትዮጵያዊ መሆን ችለዋል፡፡

ከ1980 ዓ.ም. ጀምሮ በክለብ ደረጃ በኢትዮጵያ ቡና የጀመሩት ኢሳያስ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሦስት ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን፣ በተጫዋችነት ዘመናቸው በአገር ሳይገደቡ ለታንዛንያው ቲፐር ለአምስት ዓመታት በፕሮፌሽናልነት መጫወት ችለዋል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በማኅበራዊ ገጹ እንደገለጸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥቂት ሰዎች ብቻ ሊያገኙት የሚችሉትን የአሠልጣኞች፣ አሠልጣኝ (ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር) ደረጃን አማኑኤል ከዓለም አቀፉ መረብ ኳስ ፌዴሬሽን አግኝተዋል፡፡

በዚህም መሠረት ከኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ዓለማየሁ ሸዋታጠቅ ቀጥሎ ሁለተኛው ኢትዮጵያዊው መሆን እንዳስቻላቸው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጠቅሷል፡፡

በዚህም መሠረት ኢንስትራክተር አማኑኤል (ሦስተኛ ደረጃ) የቮሊቦል አሠልጣኝነት ሰርተፍኬት ያላቸው ብቸኛ ኢትዮጵያዊ አሠልጣኝ መሆናቸውን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል።

ከተጫዋችነት በኋላ በአሠልጣኝነት ያገለገሉ ሲሆን፣ የአሠልጣኝነት ሥልጠናዎችን በአገር አቀፍ ደረጃ መስጠታቸው ተብራርቷል፡፡

በታንዛኒያ ቆይታቸውም በታንዛኒያው ቲፐርና ሜትሮ ክለቦች ከመጫወታቸው በላይ  የታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድንን ማሠልጠን ችለዋል፡፡ አማኑኤል ከታንዛኒያ መልስ በኢትዮጵያ ሙገር ሲሚንቶና ወላይታ ድቻን ማሠልጠን የቻሉ ሲሆን፣ ከድቻ ጋር ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

በአሁኑ ሰዓትም ወላይታ ድቻን በዋና አሠልጣኝነት እየመሩ መሆኑን የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።

መረብ ኳስ በኢትዮጵያ ከ1950ዎቹ ጅምሮ ተወዳጅ ከሆኑ ስፖርቶች አንዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በአኅጉር አቀፍ ውድድሮች በወንዶችና በሴቶች ምድብ እስከ 1990ዎቹ መጨረሻ ድረስ ትሳተፍ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ጊዜ መረብ ኳስ በኢትዮጵያ ያለው ተመልካች ቁጥር እምብዛም ቢሆንም ዓመታዊ ውድድሩን ያከናውናል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...