Monday, February 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹በሰሜኑ የወረደው እርቅና ሰላም በምዕራቡም ዕውን እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን አሁንም ጥሪ ታደርጋለች››...

‹‹በሰሜኑ የወረደው እርቅና ሰላም በምዕራቡም ዕውን እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን አሁንም ጥሪ ታደርጋለች›› ቄስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት

ቀን:

የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓልን በየዓመቱ የምናከብረው ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ ያለውን ታላቅ ፍቅር የገለጸበትና ቅዱስ ትዕዛዙን በመተላለፍ በኃጢአት የወደቀውን የሰው ልጅ ከራሱ ጋር ያስታረቀበትን መለኮታዊ የማዳን ሥራ ምሥጋና በተሞላ መንፈስ ለማሰብ ነው፡፡

የክርስቶስ ልደት በዓል አንድ የሚያስታውሰንና የሚያስተምረን መሠረታዊ ቁም ነገር እርቅና ሰላምን ተግቶ መፈለግንና ለዚህም የሚገባውን ዋጋ ለመክፈል መወሰን ነው፡፡ …

የክርስቶስን ልደት ስናከብር የክርስቶስን ፈለግ ከመከተል ያለፈ ምንም ነገር የለም፡፡ በተለይም ምድራችን ሰላምንና መረጋጋትን እጅግ በተጠማችበት ወቅት ልዩነትንና የልዩነትን ክፉ ውጤት ለማስቀረት መከፈል ከሚገባው ዋጋ ውጪ ምን ሊከፈል ይገባል? ሰላምና አንድነት ለበዓሉ አከባበር ስንል ከምንከፍለው ዋጋና ከምንሰጠው ትኩረት እጅጉን የላቀ ሊሆን ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በአገራችን በሰሜኑ ክፍል በተለይም በትግራይ ክልል የነበረው ጦርነት በምክክር፣ በሰላምና በእርቅ እንዲቆም ጥሪ ስታቀርብ እንደነበረች ይታወቃል፡፡ የምዕመናኑን ጸሎትና ምልጃ የሚሰማው አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ስላደረገ ክብር ምሥጋና ለእርሱ ብቻ ይሁን እንላለን፡፡ በጦርነቱ ብዙ ዋጋ ተከፍሏል፣ ለእርቁ የተከፈለው ዋጋ እና ይህንንም ተከትሎ የሚመጣው በረከት ግን በእጅጉ የላቀ ነው፡፡

የተጀመረውም የሰላም ስምምነት አፈጻጸሙም በሚገባ ተተግብሮ የእርስ በእርስ እልቂት እንዲቆም፣ የሰብዓዊ ድጋፎች፣ የመድኃኒት አቅርቦቶች፣ የተለያዩ ፋሲሊቲዎች አሁን ከጅምሩ እንደታየው እስከ መጨረሻ ድረስ በደንብ እንዲከናወኑ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡ በሒደቱም በትኩረት ትሳተፋለች፡፡

በሌላም በኩል በምዕራቡና በደቡቡ የአገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአራቱም የወለጋ ዞኖች ያለው የፀጥታ ችግር፣ በየዕለቱ የሚፈሰው የንፁሐን ደምና የሚጠፋው የዜጎች ሕይወት፣ የሚወድመው የመንግሥትና የግለሰቦች ንብረት ጉዳይ ከወትሮው በተለየ መልኩ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ቤተ ክርስቲያን ትገነዘባለች፡፡ ስለዚህም በሰሜኑ ክፍል የሚታየው የኃላፊነት መንፈስ የተሞላው የእርቅና የሰላም ድርድር በዚህም አካባቢ እውን እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን አሁንም ጥሪ ታደርጋለች፡፡

በአሁኑ ሰዓትም በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ከተፈጠሩት አለመግባባቶች የተነሳ ቁጥራቸው በርካታ የሆነ ሕዝቦች ከሚኖሩበት አከባቢ ተፈናቅለው በከባድ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም ሁሉም የአገራችን ሕዝቦች በመረባረብ የመጠለያ እና የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ቤተ ክርስቲያን አሁንም በድጋሚ ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን መካነ ኢየሱስም የአደጋው ሰለባ የሆነችባቸው ሁኔታዎች እየተከሰቱ ናቸው፡፡ በተለይም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ወለጋ በሳሲጋ ወረዳ በጋሉ ቀበሌ በሚገኘው ሙለታ ጌላ በመባል በሚታወቀው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ማኅበረ ምዕመናን አማኞች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሂዷል፡፡ ከዚህም የተነሳ ቤተ ክርስቲያን ሐዘኗን ገልጻለች፡፡ መሰል የሆኑ ድርጊቶች እንዳይከናወኑ ከመንግሥትና ከሕዝብ ሰፊ ሥራ መሠራት እንዳለበትም ቤተ ክርስቲያን ያኔም አሳስባለች፣ አሁንም ቀጥላ ለማስታወስ ትወዳለች፡፡

በመጨረሻም ይህንን በዓል ስናከብር እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠልንን ታላቅ ፍቅሩንና በቸርነቱ ያደለንን ጸጋ እያሰብን እኛም ከእርሱ ከተቀበልነው በረከት ለሌሎች በቸርነት ማካፈል ክርስቲያናዊ ኃላፊነታችን እንደሆነ ልንገነዘበው ይገባል፡፡

በዚህ የበዓል ወቅትም ሆነ በሌሎች ጊዜያት ሁሉ ችግር የደረሰባቸውን ወገኖች በተለይም ተንከባካቢና አሳዳጊ የሌላቸውን ሕጻናት፣ አቅመ ደካሞችን፣ አረጋዊያንን፣ እንዲሁም ሕሙማንን፣ በድኅነት የሚማቅቁ፣ ተፈናቅለው የሚገኙ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ወገኖችን ልናስባቸውና ልንደርስላቸው እንደሚገባም በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...