Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹ለሰላም በተገባው ቃል መሠረት አፈጻጸሙ በሕዝቦች ቀና ግንኙነት እንዲመሠረት ተባብሮ መሥራት ያስፈልገናል››...

‹‹ለሰላም በተገባው ቃል መሠረት አፈጻጸሙ በሕዝቦች ቀና ግንኙነት እንዲመሠረት ተባብሮ መሥራት ያስፈልገናል›› የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ

ቀን:

የገና በዓል እውነተኛ ትርጉም የሚኖረው ሰው ከራስ ወዳድነት ሲወጣ ነው፡፡ የገና በዓል የሚደምቀው የሌሎችንም ደስታ በመፈለግ ነው፡፡ የገና በዓል ቆም ብለን ራሳችንን፣ ማኅበረሰባችንን እንድንመረምር ሊጋብዘን ይገባል፡፡

አምላክ ስለፍጥረታቱ ግድ ስለሚለው በአዕምሮ ልንረዳው የማንችለው ነገር ተከሰተ፣ የተዓምራት ተዓምር ተፈጸመ፡፡ አምላክ የሰውን ልጅ ከማፍቀሩ የተነሳ ደስታውንና ሐዘኑን መካፈል ፈቀደ፣ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ፈጥሮ ልዩ ማዕረግ ሰጠው፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅ በተደጋጋሚ ይህንን ክብር ሲረሳ፣ አመፀንም ሲመርጥ ይታያል፡፡ በትዕቢት ፈተና ይወድቃል፡፡ ያለ እግዚአብሔር እንደ እግዚአብሔር መሆን ይፈልጋል፡፡ ያለ ፈጣሪ ፈቃድ ሁሉን መወሰን ይፈልጋል፡፡ ለአምላክ ቦታ ሳይሰጥ የሥነ ምግባርን ምስጢር መቆጣጠር ይሻል፡፡ ያለ ፈርሃ እግዚአብሔር ማስተዳደር ይመኛል፡፡ ነገር ግን ማዕረግ ሲባል ኃላፊነትም እንዳለ መርሳት አይገባም፡፡

ይህም ለሰው ልጅ የተሰጠው ክብርና ኃላፊነት ይበልጥ በወልድ አምላክ አማካይነት ተረጋገጠ፡፡ ሰው ከውድቀት ይነሳም ዘንድ ወልድ አምላክ ወደታች መጣ፡፡ ሰው የሚገኝበት አዝቅት ድረስ ወረደ፡፡ ይህም ሰውን ወደ ከፍታ ሊያወጣው ሲል ነው፡፡ በገና ሚስጢር ጥበብ ሥጋ ለበሰች ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጥበብ ነውና፡፡ በገና ምስጢር የመለኮታዊ ፍቅር ልደት ነው የምናከብረው፡፡ እሱ የሰላም አለቃ ነውና፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እግዚአብሔር በተለያዩ ነብያት አማካይነት ፈቃዱን ይገልጽ እንደነበረ ቅዱሳት መጽሐፍት ያስተምሩናል፡፡ ትንቢቱም ወደ ሰላምና ወደ ፍትሕ የሚጠራ ነው፡፡ ሕዝቡ ሲያዝን የሚያጽናና፣ ሕዝቡ አምላኩን ሲረሳ፣ ፍትህን ሲያጓድል፣ ንጽህናን ሲበድል ድግሞ ወደ ንስሐ የሚጠራ መልዕክት አንደ ነበር ነብዩ በእግዚአብሔር ስም ይናገራል፡፡

የተከበራችሁ የአገራችን ሕዝቦች እግዚአብሔር በጊዜው ፀሎታችንን ሰምቶ የሰላም ድርድሩ በመግባባት መንፈስ በመፈጸሙ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ለአገር ሰላምና ለሕዝቦች ደኅንነት በተገባው ቃል መሠረት የአፈጻጸሙ ድርጊት ተገዥ በመሆን ለመላው ሕዝባችንና በግጭቱ ዙሪያ ለሚገኙ ወገኖች ዘላቂ ሰላምና የሕዝቦች ቀና ግንኙነት እንዲመሠረት በአዲስ ምዕራፍ ተባብሮ መሥራት ያስፈልገናል፡፡ ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልን፡፡

በጸሎት አስታውሱን የሚሉን ብዙ ወገኖቻችን በተለይ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚያደርጉት ጉዞ በብዙ ቦታዎች የሚንገላቱት፣ በባዕድ ሀገር የሚታሰሩት፣ ተስፋ በማጣት የሚጨነቁት፣ ሞተው በድብቅ በጅምላ በየሀገሩ የሚቀበሩት፣ እንዲሁም በአንዳንድ ዓረብ አገሮች ታስረው ከተንገላቱ በኋላ ወደ አገራቸው የሚመለሱትን ወገኖች ማስታወስና መርዳት በመልሶም ማቋቋም ልንደግፋቸው ይገባል፡፡

በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ምን ያስፈልጋቸዋል? ምን ጎደላቸው? ቁስላቸው እንዴት ሊታከም ይችላል? በማለት በብቸኝነት የሚገኙትን፣ የተገለሉትን፣ የአልጋ ቁራኛ የሆኑትንና አቅመ ደካሞችን ሁልጊዜ ማስታወስ ይገባል፡፡ እያንዳንዱ የአቅሙን ሲያበረክት ነው ወደ ትልቅ ውጤት የሚደረሰው፡፡ በወንጌል አንዲት መበለት የሰጠችው ሳንቲም ብዙ ሃብታሞች ከሰጡት የበለጠ የክርስቶስን ትኩረት እንደሳበ እናነባለን፡፡ የሰው ሕይወት በቁሳዊ መለኪያ ብቻ አይለካም፣ ሰላምና ጤናም በገንዘብ አይገዛም፡፡ በእርግጥ በገንዘብ ብዙ ነገሮች መሥራት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ገንዘብን እንደ ዋና ሐሳባችን ስናደርግ ወሳኝ የሆኑ ቁም ነገሮችን የመርሳት አደጋ ላይ እንወድቃለን፡፡  ማስተዋል ያለብን የአንድ ማኅበረሰብ ትልቁ እሴት በቅንነት መተሳሰብ ነው፡፡ ሰላምንና ፍቅርን ማትረፍ ገንዘብን ከማትረፍ ይበልጣል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...