Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየሦስት ጊዜ ኦሊምፒክ ሻምፒዮኗ ጥሩነሽ ዲባባ ከአራት ዓመት በኋላ ወደ ውድድር ትመለሳለች

የሦስት ጊዜ ኦሊምፒክ ሻምፒዮኗ ጥሩነሽ ዲባባ ከአራት ዓመት በኋላ ወደ ውድድር ትመለሳለች

ቀን:

የረዥም ርቀት ንግሥቷ ጥሩነሽ ዲባባ ከአራት ዓመት በኋላ ወደ ውድድር እንደምትመለስ ታውቋል፡፡ እ.ኤ.አ. 2018 ለመጨረሻ ጊዜ ውድድር ላይ የተካፈለችው የሦስት ጊዜ የኦሊምፒከ ሻምፒዮናና የአምስት የዓለም ሻምፒዮናዎች ፈርጥ በአርማኮ ሂውስተን ግማሽ ማራቶን እንደምትወዳደር ተገልጿል፡፡

ጥሩነሽ ከረዥም ጊዜ በኋላ ወደ ውድድር ስትመለስ የመጀመሪያ የጎዳና ላይ ተሳትፎዋን በሂውስተን ግማሽ ማራቶን እሑድ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ታደርጋለች፡፡ ከአራት ዓመት በፊት የመጨረሻ ውድድሯን ያከናወነችው ጥሩነሽ በወሊድና በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከውድድሮች ርቃ የቆየች ሲሆን፣ በ2023 በተለያዩ አገሮች በሚከናወኑ የዓለም አቀፍ የጎዳና ውድድሮች ላይ ትሳታፋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በርካታ ገድሎችን በትራክ ውድድች ላይ ማስመዝገብ የቻለችው ጥሩነሽ፣ በጎዳና ውድድሩም አዲስ ታሪክ ልጽትፍ እንደምትችል ይታመናል፡፡ የግማሽ ማራቶን ምርጥ ጊዜዋ ከአምስት ዓመት በፊት የገባችበት 66.50 ደቂቃ ነው፡፡

‹‹ሂውስተን የምወደው የውድድር ቦታ ነው፣ ዝግጅቴም በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው፣ ያለኝን አቅም ለመፈተሽና የቀጣይ የአትሌቲክስ ሕይወቴን ምዕራፍ ለመወሰን ይህ መልካም አጋጣሚ ነው፤›› በማለት ጥሩነሽ አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡

እ.ኤ.አ. በ2017 በለንደን የዓለም ሻምፒዮና 10 ሺሕ ሜትር ርቀት የብር ሜዳልያ ማሳካት የቻለችው ጥሩነሽ፣ በዚያው ሰሞን በቺካጎ ማራቶን 2፡18፡30 በመግባት በአንደኝነት ማጠናቀቅ ችላለች፡፡ ከወራት ቆይታም በቫሌንሽያ ሳን ሲሊቪስትሪ ማድሪድ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር በ30፡40 በመሮጥ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ካጠናቀቀች በኋላ ላለፉት አራት ዓመታት ከውድድር ርቃ ሰንብታለች፡፡

በትራክ ውድድሮች በርካታ ድሎች መጎናጸፍ የቻለችው ጥሩነሽ በማራቶን በርካታ ውድድሮችን ላይ እንደምትሳተፍ ይጠበቃል፡፡ ከዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ውድድር የተመለሰችው ጥሩነሽ፣ ከወሊድ በኋላ በቂ ዝግጅት ስታደርግ እንደነበርም ተነግሯል፡፡

‹‹የመካከለኛና የረዥም ርቀት ንግሥት›› ሆና ያሳለፈችው ጥሩነሽ፣ ካሸነፈቻቸው  ውድድሮች በዓለም አትሌቲክስ በወርቅ ደረጃ ከሚታወቁ ማራቶኖች አንዱ የሆነው የቺካጎ ማራቶን ይጠቀሳል፡፡

ሦስት ኦሊምፒኮችን ጨምሮ ባደረገቻቸው የተለያዩ የረዥም ርቀት የሩጫ ውድድሮች በአሸናፊነት የዘለቀችው ጥሩነሽ ዲባባ በእንግሊዝ በተከናወነው የግሬት ሳውዝ ራን የ10 ማይል ሩጫንም በማሸነፍ ትታወቃለች፡፡ በውድድሩ ኃይሌ ገብረሥላሴን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈውበታል፡፡

ጥሩነሽ በአትሌቲክስ ታሪክ ወጣቷ የዓለም ሻምፒዮን ለመሆን የቻለች ሲሆን፣ የኦሊምፒክ 5,000 ሜ እና 10,000 ሜ የመጀመርያዋ ድርብ ባለ ድል ከመሆኗ ባለፈም፣ በተከታታይ በረዥም ርቀት በማሸነፍም የመጀመርያዋ ተጠቃሽ ናት፡፡ የኦሊምፒክ ሦስት ጊዜ፣ የዓለም ሻምፒዮና 5 ጊዜ ባለ ወርቅ፣ በዓለም ሻምፒዮና 1 ባለ ብር ሜዳሊያ፣ 3 የኦሊምፒክ ነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኗም ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩልም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የጎዳና ውድድሮች እየታየች የምትገኘው የጥሩነሽ ዲባባ ታናሽ እህት አና ዲባባም በዘንድሮው ሂውስተን ግማሽ ማራቶን ከእህቷ ጋር እንደምትወዳደር የውድድሩ አዘጋጅ ይፋ አድርጓል፡፡ በ1,500 ሜትር እንዲሁም 5,000 ሜትር ርቀቶች ላይ በመካፈል በሩጫ የእህቶቿን ፈለግ የተከተለችው አና፣ በተለያዩ የጎዳና ውድድሮች ላይ መሳተፏን ቀጥላለች፡፡

በ2020 በስፔን ባርሴሎና በ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድሯን የጀመረችው አና፣ ዘንድሮ በአሜሪካ ቻርሌስትን 10 ኪሎ ሜትር ውድድር በመሳተፍ  32፡37 በማጠናቀቅ የግል ምርጥ ሰዓቷን በስሟ ማስመዝገብ ችላለች፡፡ በቅርቡም በአሜሪካ ፔትርስበርግ ግማሽ ማራቶን በመካፈል 1፡14፡09 የገባችበት ሰዓት የቅርብ ጊዜ ውጤቷ ነው፡፡

ከሁለቱ እህትማማቾች ጎን ለጎን በ2021 የበርሊን ማራቶን ሁለተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ኢትዮጵያዊቷ ሕይወት ገብረኪዳን (ምርጥ ጊዜዋ 66:47 ደቂቃ) እንደምትካፈል ይጠበቃል፡፡ የ2022 የዓለም ሻምፒዮና ላይ አራተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው ኤርትራዊቷ ናዝሬት ወልዱም በዘንድሮው ሂውስተን ግማሽ ማራቶን ትጠበቃለች፡፡

ሂውስተን የዓለም አትሌቲክስን ሁለት የወርቅ ደረጃ ማራቶን ውድድር ማሰናዳት የቻለች አዘጋጅ ናት፡፡ በእነዚህ ሁለት ውድድሮች 27,000 ተካፋዮች ሲኖሩት፣ ተጨማሪ 6,000 ተካፋዮች የሚሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የጎዳና ሩጫ ውድድሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ መበራከታቸውን ተከትሎ፣ አትሌቶችም ፊታቸውን ወደ ማራቶን እያዞሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህም በቤት ውስጥ ውድድሮች ይልቅ በጎዳና ላይ የሚደረጉ ውድድሮች ቁጥር ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱን የዓለም አትሌቲክስ ይፋ አድርጓል፡፡

የዓለም አትሌቲክስ በ2023 እንደሚከናወኑ ይፋ ካደረጋቸው የጎዳና ውድድሮች ከ200 የሚልቁ ሲሆን፣ ዘንድሮ ከ20 በላይ አዳዲስ ውድድሮች መጨመራቸውን አሳውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...