የፖለቲካ የገበያ ቦታ ከተቋማዊ ሙስና፣ በወንጀለኞች ተጠልፎ ከተያዘ የሌቦች አገዛዝ፣ የጦር አበጋዝነትና የጦርነት ኢኮኖሚዎች ጋር በቅርበት የሚዛመድ መሆኑን ይገልጻል። ሙስና ከፖለቲካ ገበያ ጋር የሚወዳጅ ቢሆንም ሁለቱ ግን የተለያዩ ባህሪ ያላቸው ክስተቶች ናቸው።
በፖለቲካ ገበያ አመክንዮ፣ ሁከት በዋናነት የመደራደሪያ ዘዴ እንደሆነ የሚገልጸው ደግሞ ተማራማሪው አሌክስ ዴዋል (ፕሮፌሰር)፣ ክፍያ ያልተፈጸመበት ሁከት ትክክለኛ ዋጋው የማይታወቅ ገንዘብ መሆኑ ልብ ሊባል እንደሚገባ በሀተታው ያስረዳል። በፖለቲካ ገበያ ውስጥ በጣም ከባድ የሆኑ ሁከቶች ብዙውን ጊዜ የሚነሱት የፖለቲካ ንግድ ተዋናዮች በሚፈጽሟቸው ስህተቶች ምክንያት ሲሆን፣ ስህተቶቹ የሚታወቁት የተፈጠረው ጥቃት የበቀል አመክንዮ እየፈጠረ ግጭቱን በማባባስ መጠነ ሰፊ እንደሚያደርገው ያስረዳል።
ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ሰሞኑን ባካሄደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) የፖለቲካ ገበያ በኢትዮጵያ መንስራፋቱን በይፋ ገልጸዋል።
ለገዥው ብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ገለጻ ሲያደርጉ የተደመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ገበያ ከጊዜ ወደ ጊዜ መልኩን እየቀየረ የብልፅግና ጉዞውን አደጋ ውስጥ የሚከት ልምምድ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምኅዳር ወሮታል ሲሉ ተደምጠዋል። ዝርዝር ዘገባውን በዚህ ሊንክ ይመልከቱ ፡፡