Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢሰመጉ መንግሥት በሠራተኞቹ ላይ የሚፈጽመውን ሕገወጥ እስርና ጫና እንዲያቆም ጠየቀ

ኢሰመጉ መንግሥት በሠራተኞቹ ላይ የሚፈጽመውን ሕገወጥ እስርና ጫና እንዲያቆም ጠየቀ

ቀን:

በኢዮብ ትኩዬ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) መንግሥት በድርጅቱ ሠራተኞች ላይ የሚፈጽመውን ሕገወጥ እስርና ጫናዎች እንዲያቆምና በእስር የሚገኙ ሠራተኞቹ እንዲፈቱ ጠየቀ፡፡

ድርጅቱ ይህን ያሳሰበው ዓለም ባንክ አካባቢ ለሥራ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አራት የድርጅቱ ሠራተኞች በፖሊስ መታሰራቸውን አስመልክቶ፣ ሐሙስ ታኅሳስ 27 ቀን 2025 ዓ.ም. ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

ሠራተኞቹ የታሰሩት በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተካሄደ ባለው ቤት የማፍረስ ዘመቻ ምክንያት፣ ቤታቸው የፈረሰባው ግለሰቦች ለኢሰመጉ ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት ጥቆማውን ለማጣራት በተንቀሳቀሱበት ወቅት መሆኑ መግለጫው አስረድቷል፡፡

በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች መንግሥት በራሱ ፈቃድ አደራጅቶ በሰጣቸው ቦታ የገነቡት መኖሪያ ቤት እንደገና በመንግሥት አካላት እየፈረሰባቸው መሆኑን ነዋሪዎቹ በማማረር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ በተለይ ዓለም ባንክ በተሰኘው አካባቢና በአዲስ አበባ ዙሪያ እንደ አዲስ እየተዋቀረ ነው በተባለው ሸገር ከተማ፣ የነዋሪዎች ቤት በመንግሥት ኃይሎች እየፈረሰ ነው ብለዋል፡፡

አቤቱታ አቅራቢዎቹ በተለይም በሱሉልታ ክፍለ ከተማ አካኮ ማና አቢቹ በሚባል ቀበሌ ተደራጅተው በሕጋዊ መንገድ በተሰጣቸው ቦታ ቤት ከገነቡ በኋላ፣ በመንግሥት አካላት ፈርሶብናል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በሱሉልታ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ቅሬታ አቅራቢዎች ከሦስት ዓመታት በፊት በሕጋዊ መንገድ መንግሥት ራሱ ቦታውን ሰጥቷቸው እንደነበር አስታውሰው፣ ከፍተኛ ወጪ አውጥተው የመኖሪያ ቤት ከገነቡ በኋላ በሕገወጥ ቤት ሠሩ ከተባሉ ሰዎች ጋር በጅምላ እየፈረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዓለም ባንክ አካባቢ የመኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ስሞታ አቅራቢዎች በበኩላቸው፣ ለተለያዩ ሚዲያዎችና ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ቢጮሁም ቤታቸው መፍረሱን ገልጸው መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

አቤቱታ አቅራቢዎቹ ለኢሰመጉ ቅሬታውን እንዳሰሙ ገልጸው፣ ድርጅቱም ሦስት የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎችና አንድ ሾፌር መታሰራቸውን፣ ግለሰቦቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት ሁነቱን እየተከታተሉ በነበሩበት ወቅት መሆኑን በመግለጫው በዝርዝር አስፍሯል፡፡

ሠራተኞቹ ዓለም ባንክ አካባቢ እየተከናወነ ነው የተባለውን ጥቆማ ለማጣራት በሄዱበት ወቅት በፖሊስ ተይዘው ያሉበትን ማወቅ ሳይቻል እንደቆየ፣ በተደጋጋሚ በተደረገ ጥረት አራቱም ሠራተኞች ዓለም ገና ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንዳገኛቸው ኢሰመጉ አስታውቋል፡፡

ኢሰመጉ በመግለጫው እንዳስረዳው ከሆነ በዓለም ገና ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩት አራት ሠራኞች በተጨማሪ፣ አንድ የድጅርቱ መኪናም ይገኝበታል፡፡

በሌሎች የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ላይ የተለያዩ ጫኛዎች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን፣ ይህም ድርጊት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት በመቋቋም በመዝገብ ቁጥር 1146 መሠረት የተመዘገበውን ኢሰመጉ ለሰብዓዊ መብት መከበር የተቋቋመበትን ዓላማ ለመፈጸም እንቅፋት የሚሆን፣ ባሙያዎቹ በነፃነት ተንቀሳቅሰው እንዳይሠሩ ለማድረግና ለማሸማቀቅ የተደረገ፣ ከሕግና አግባብ ውጪ የሆነ ድርጊት መሆኑን ኢሰመጉ በመግለጫው አስፍሯል፡፡

በመሆኑም መንግሥት በኢሰመጉ ላይ ሕገወጥ እስርና የተለያዩ ጫናዎችን ከመፈጸም እንዲቆጠብ፣ በእስር ላይ የሚገኙ ሠራተኞችን ፖሊስ በአስቸኳይ ከእስር እዲፈታ ጠይቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...