- ጎሽ እንኳን መጣህ።
- ምነው?
- እኔማ ሕዝቡ ብቻ ነበር የተማረረ የሚመስለኝ።
- በምን?
- በዋጋ ንረት።
- ዋጋ ንረትን ምን አመጣው?
- ይኸው አለቃችሁ አስሬ የፖለቲካ ማርኬት፣ የፖለቲካ ሸቀጥ እያሉ በምሬት ሲያወሩ አትሰማም እንዴ።
- እ… እሱን ነው እንዴ?!
- በእርግጥ ፖለቲካ እንደሚሸጥ አላውቅም ነበር። ግን ስንት ቢገባ ነው እንዲህ የተማረሩት?
- ኧረ ተይኝ… በጣም ንሯል።
- የምርት እጥረት ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለው?
- ሁለቱም ነው።
- ምን እና ምን?
- የምርት እጥረቱ እንደኛው ነው።
- ሌላውስ?
- ሌላውማ ሕገወጥ ደላላውና በአቋራጭ ለመክበር የሚጥሩ ነጋዴዎች መኖራቸው ነው።
- እዚያም እንደዚህ አለ?
- ኧረ እንደውም ዋናዎቹ እዚህ ነው ያሉት።
- ታዲያ ከውጭ ለምን አታስመጡም?
- አይ እሱማ አይሆንም። ምንዛሬውም የለም።
- ካልሆነ ቢያንስ ዋጋውን ለማረጋጋት አልሞከራችሁም?
- እንዴት ብለን? ተቸገርን እኮ?
- እንዴት? ቢያንስ ማቋቋም ያቅታችኋል?
- ምን ማቋቋም?
- የእሑድ ገበያ!
[ለቀናት ከቢሮ የጠፉት የሰላም ስምምነቱን አተገባበር የሚከታተሉት ክቡር ሚኒስትር ወደ ቢሮ ተመልሰዋል። አማካሪያቸውም በተቋማዊ ጉዳዮች ላይ ሪፖርት ማቅረቡን ትቶ ስለ ሰላም ስምምነቱ አተገባበር እየጠየቃቸው ነው]
- ክቡር ሚኒስትር እውነት ይህ የሰላም ስምምነት የሚሳካ ይመስሎታል?
- ለምን ተጠራጠርክ?
- የሰላም ስምምነቱን ተቀብለው ቢፈርሙም የታጠቀ ኃይላቸውን ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር አቅም ያላቸው አልመሰለኝም።
- ለምን እንደዛ አልክ?
- ከአንዳንድ የውጭ ተቋማት ጓደኞቼ ከምሰማው መረጃ እንደዚያ የሚሆን አልመስል አለኝ። በተጨማሪም…
- እ… በተጨማሪ ምን?
- የተወሰኑ ታጣቂዎች አፈንግጠዋል የሚል ወሬ ሰምቻለሁ።
- በእርግጥ የሰላም ስምምነቱን ያልተቀበሉ ታጣቂዎች እንዳሉ ይታወቃል። በሌላ በኩል ደግሞ….
- አየሰማሁ ነው… ይቀጥሉ
- የተወሰኑ ኃይሎች ትጠቃቸውን እንደያዙ እየተበተኑና አንዳንዶቹም መሣሪያ እንደያዙ ወደ ቤተሰባቸው እየሄዱ መሆኑን ሰምተናል።
- እንዴ! ታዲያ ይኼ ትክልል ነው?
- እኛም እርስ በርሳቸው እንዳይጋጩና በነዋሪዎች ላይ ውንብድና እንዳይፈጽሙ ሠግተናል።
- ክቡር ሚኒስትር ምሽግ የሚቆፍሩ እንደሆነም እኮ እየተወራ ነው?
- አሱንም ሰምተናል።
- ታዲያ ይኼ ልክ ነው?
- እኛም ትክክል እንዳልሆነ በመግለጽ በታዛቢዎች ፊት ማብራሪያ ጠይቀናል።
- ምን ምላሽ ሰጡ?
- የታጠቀ ጦርን ካልተዋጋ ችግር ሊፈጥር ይችላል ነው የሚሉት።
- ስለዚህ?
- እኛ ሌላ ፍላጎት የለንም ነው የሚሉት።
- ታዲያ ምሽግ የሚያስቆፍሩት ለምንድን ነው?
- ከውጊያ ቀጠና በድንገት የወጣ ወታደር በሥራ ካልተጠመደ ያልተገባ ነገር ሊያስብ ስለሚችል ምሽግ እንዲቆፍሩ ማድረጋቸውን ነው የገለጹልን።
- በታዛቢዎች ፊት እንደዚያ ያሉት?
- አዎ።
- እና እናንተ ይህንን አምናችሁ ተቀበላችሁ?
- እኛ ሙሉ እምነት ባይኖረንም ምንም እንደማያመጡ ስለምናውቅ ብዙ አልተጨንቀንም። ግን …
- እየሰማሁ ነው… ይቀጥሉ ክቡር ሚኒስትር?
- በተወሰነ ደረጃ ምክንያታቸው ትክክል እንደሆነ እናምናለን።
- ለምን?
- ምክንያቱም ሥጋት አላቸው።
- የምን ሥጋት?
- እሱን መገመት ትችላለህ።
- ገባኝ ገባኝ።
- ምንድነው የገባህ?
- ሥጋታቸው ምን እንደሆነ።
- ምንድነው?
- ታጣቂዎቹ አንድ ነገር ይሞክራሉ ብለው ፈርተዋል።
- ምን ሊሞክሩ ይችላሉ?
- ፈንቅል!
|
|