የፊፋ ፕሬዚዳት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ፣ ባለፈው ሐሙስ ታኅሣሥ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በ82 ዓመቱ ባረፈው የእግር ኳሱ ንጉሥ ብራዚላዊው ፔሌ ሥርዓተ ስንብት ላይ ለጋዜጠኞች የተናገሩት፡፡ የፔሌን ልዕልና ያስታወሱት ኢንፋንቲኖ ምክንያቱንም ሲገልጹ፣ ከመቶ ዓመት በኋላ ልጆች ፔሌ ማን እንደነበረ ሲጠይቁ፣ በጥሩ መንፈስ እሱን ማስታወስ ስላለባቸው ነው ብለዋል፡፡ በዓለም ዙሪያ ሕፃናት፣ ወንዶች እና ሴቶች በሚጫወቱበት የእግር ኳስ ሜዳ ውስጥ ጎል በሚያስቆጥሩበት ጊዜ እርሱን ማስታወስ አለባቸው ሲሉም አክለዋል። ይህ እንደሚሆንም ማረጋገጥ አለብን፡፡