በዘጠና ሦስት ዓመት የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ታሪክ ሦስት ጊዜ ዋንጫውን በመውሰድ ብቸኛ የሆነው ፔሌ ሥርዓተ ቀብር ታኅሣሥ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በትውልድ ስፍራው ሳንቶስ ተፈጽሟል፡፡ በዋዜማው በቪላ ቤልሚሮ ስታዲየም መሀል የተቀመጠውን አስክሬኑን ብራዚላውያንና የፊፋ ፕሬዚዳት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ጨምሮ እንግዶች ተሰናብተውታል፡፡ ዲደብሊው እንደዘገበው፣ በሥርዓተ ቀብሩ መርሐ ግብር መሠረትም አስክሬኑ ያለፈው በሕይወት በሚገኙት የ100 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋዋ የፔሌ እናት ሴሌስቴ ናሲሜንቶ ቤት በኩል ነው፡፡ በስንብት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የፔሌ 10 ቁጥር ማሊያ ለገበያ ቀርቦ ነበር፡፡ ፎቶዎቹ የስንብት ሥነ ሥርዓቱን በከፊል ያሳያሉ፡፡
ፎቶ ስካይ ሰፖርትስ