Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ‹‹ራስን ማወቅ የመጨረሻ ጥበብ››

‹‹ራስን ማወቅ የመጨረሻ ጥበብ››

ቀን:

  • የሰው ልጅ የተፈጥሮን ሕግ ሊለውጥ አይችልም። ለምሳሌ ቀንና ጨለማን፣ ሞትና ሕይወትን፣ ማደግና ማርጀትን፣ ማበብና መክሰምን ሊለውጥ አይችልም። የማይለወጡ የተፈጥሮ ሕግጋት አሉ ማለት ነው። እነዚህን አሜን ብሎ መቀበል አንዱ የደስታ ምንጭ ማለት ነው። አሜን ብሎ ተቀብሎ ዝም ማለት ብቻ አይደለም።
  • የሕይወት መጨረሻ ግቡ የሰው ልጅ በዚህች አለም ላይ በሚኖርበት አጭር ጊዜ ውስጥ ተፈጥሮውን አሟልቶና ተደስቶ ለመኖር ስለሆነ፤ እያንዳንዱ ሰው ተፈጥሮውን እንዳያሟላና እንዳይደሰት የሚያደርጉትን መጥፎ ነገሮች ሁሉ ከራሱ ልብ ውስጥም ሆነ ከአካባቢው ለማስወገድ መጣር አለበት። ይህን ለማድረግ… ልበ ሙሉ መሆን ያስፈልጋል።
  • የሰው ልጅ ክብር ዋስትና መስዋዕትነት ነው። መስዋዕትነት ደግሞ ያለ ልበ ሙሉነት መች ይሆናል። ራሳቸው እየነደዱ አልቀው ለሌላው ብርኃን የሚሆኑ ልበ ሙሉዎች ብቻ ናቸው። መጽሐፉም’ኮ እሹ ታገኛላችሁ፣ አንኳኩ ይከፈትላችኋል ያለው ሌላ ሳይሆን የራሳችንን ልብ ነው። ራስን ማወቅ የመጨረሻ ጥበብ ነው።
  • ራስን ማወቅ ሌላውንም ማወቅ ይሆናል። ካወቅክ ዘንድ ለራስህ የምትሻውን ለሌላውም ትመኛለህ። ለራስህና ለሰው ልጅ ሁሉ በጎ ፈቃድና ፍቅር ይኖርሃል። ከዚህ ዕውቀት ደረጃ ላይ ስትደርስ ለምታደርገው ነገር ሁሉ ምሥጋናም ሆነ ጥቅም ከሰው ዘንድ አትሻም። ልብህ ጥቅም ላይ ካተኮረ የተፈጥሮን በጎ ምግባር ትስታለህ።
  • በዓሉ ግርማ ‹‹ደራሲው›› (1972)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...