ከሲኣት
ትንሿ እህቴ ከሩቅ እየተጣራች መጣች
‹‹እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ››
እናታችን ለጨረሩ መከላከያ መዳፏን ግንባሯ ላይ አጋድማ
‹‹ምነው? ምን ሆንሽ?›› አለች
‹‹ዱላ ስጪኝ ዱላ ስጪኝ››
‹‹ምነው? ለምንሽ?››
‹‹አለቃ ተመረጥኩ››
ዱላ አሳጥራ ሰጠቻት።
. . .
አመሻሽ
ትንሿ እህቴ እያለቀሰች
‹‹እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ››
እናታችን ‹‹ምነው? ምን ሆንሽ?››
‹‹ከአለቃነት ተሻርኩ››
- ዓለማየሁ ገላጋይ ‹‹ውልብታ››