Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዋሊያዎቹ ለቻን ውድድር ቅድመ ዝግጅታቸውን ነገ ይጀምራሉ

ዋሊያዎቹ ለቻን ውድድር ቅድመ ዝግጅታቸውን ነገ ይጀምራሉ

ቀን:

  • የውድድሩ መርሐ ግብር ላይ ማሻሻያ ተደርጓል

በአልጄሪያ አዘጋጅነት ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) ውድድር ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጀቱን ሐሙስ ታኅሣሥ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደሚጀምር ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት በድሬዳዋ ስታዲየም መጠናቀቃቸውን ተከትሎ፣ ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገላቸው 28 ተጫዋቾች ከማክሰኞ ታኅሣሥ 18 ቀን ጀምሮ ወደ ሆቴል መግባታቸው ተገልጿል፡፡ ዛሬ ረቡዕ ታኅሣሥ 19 ቀን ሙሉ የጤና ምርመራ ካደረጉ በኋላ ሐሙስ መደበኛ ልምምዳቸውን እንደሚጀምሩ ታውቋል፡፡

በምድብ አንድ ከአስተናጋጇ አልጄሪያ፣ ሞዛምቢክና ሊቢያ ጋር የተደለደለው የዋሊያዎቹ ስብስብ የመጀመሪያ ሳምንት ዝግጅቱን በአዲስ አበባ ካደረገ ከአንድ ሳምንት በኋላ፣ ቀጣይ ዝግጅቱን ሞሮኮ ላይ እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን፣ አንድ የአቋም መለኪያ ጨዋታውን በዚያው እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ ከየትኛው ብሔራዊ ቡድን ጋር ጨዋታውን እንደሚያደርግ ግን አልተገለጸም፡፡

ከጥር 5 እስከ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በአልጄሪያ አራት ከተሞች የሚከናወነው የቻን ሻምፒዮና ቀድሞ የወጣው መርሐ ግብር ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡ በዚህም መሠረት መጀመሪያ ይፋ በሆነው መርሐ ግብር መሠረት፣ በመክፈቻው ዕለት ሊደረግ ታስቦ የነበረው የኢትዮጵያና የሞዛምፒክ ጨዋታ ወደ ጥር 6 ቀን መዘዋወሩ ተገልጿል፡፡ በመክፈቻው ዕለት አዘጋጇ አልጀሪያ ከሊቢያ በሚያደርጉት ብቸኛ ጨዋታ ሻምፒዮናው በይፋ ይጀምራል፡፡ 

በዘንድሮ የአፍሪካ አገሮች ሻምፒዮና ላይ 18 ብሔራዊ ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ተካፋይ አገሮች መደበኛ ልምምዳቸውን መጀመራቸውን ታውቋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 የጀመረው ቻን ውድድር አገር በቀል የሆኑ ተጫዋቾች ብቻ ይካፈሉበታል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በውድድሩ ላይ ለመካፈል አስተዳደራዊ ዝግጅቶችን እያደረገ እንደሚገኝ ገልጾ፣ ከውድድሩ ጋር ተያያዥ ለሆኑ ወጪዎች ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም የሚያስፈልግ በመሆኑ፣ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ፌዴሬሽኑ ላቀረበው ጥያቄ መንግሥት የሰጠውን ምላሽ ለማወቅ ሪፖርተር ከፌዴሬሽኑ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለመንግሥት ካቀረበው ጥያቄ ባሻገር፣ የተለያዩ የገቢ አማራጮችን እየተመለከተና አጋር ተቋማትን እያፈላለገ እንደሆነ ቢያብራራም፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ይፋ ያደረገው የአጋርነት ስምምነት የለም፡፡

በኢትዮጵያ 27 ፌዴሬሽኖች ውስጥ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቀጥሎ የፋይናንስ አቅሙን በማጠንከር የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በፋይናንስ እጥረት የመንግሥት ደጅ በተደጋጋሚ ሲጠና እየተስተዋለ ነው፡፡

ባለፈው ነሐሴ ለሁለተኛ ጊዜ ምርጫውን አሸንፎ የተረከበው የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ፣ የፌዴሬሽኑን የፋይናንስ አቅም እንደሚያጎለብት ቃል መግባቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በቀጣይ ከተለያዩ አጋር ተቋማትን በማፍራት የፋይናንስ ችግሩን ፈቶ፣ የመንግሥት ድጋፍ ከመጠባበቅ ይላቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከዚህ ቀደም ከተለያዩ ተቋማት ጋር የአጋርነት ስምምነት ቢያስርም፣ ከጥቂቶቹ ጋር መዝለቅ ሳይችል ውሉን ማቋረጡ ይታወሳል፡፡ በዚህም ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የፋይናንስ አቅሙን ከማጎልበት አንፃር የተለያዩ አማራጮችን ከመፈለግ አንፃር ክፍተቶች እንዳሉበት ሲነገር ከርሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...