Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየረዥም ጊዜ የዲፕሎማቶች አገልግሎት ሽልማት ሊጀምር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

የረዥም ጊዜ የዲፕሎማቶች አገልግሎት ሽልማት ሊጀምር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ቀን:

በውጭ ግንኙነት ዘርፍ ለረዥም ዓመታት አገልግሎት የሰጡና በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ ዲፕሎማቶችን ለመሸለምና የዲፕሎማቶች ክለብ ለማቋቋም፣ ኮሚቴ መሥርቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኰንን ታኅሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በተጀመረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋናው መሥሪያ ቤትና ተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና የሚሲዮን መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ ለኢትዮጵያ ክብር በውጭ አገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ዲፕሎማቶች የሚሰጥ ሽልማት ለማስጀመር ሥራ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የዲፕሎማቶች ክለብ የማቋቋምና ሽልማት የመስጠት ተግባር በነባርና በአዲስ ገቢ ዲፕሎማቶች መካከል የተሳሰረ ቀጣይ ታሪክ እንዲኖር ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን በመጥቀስ፣ ለዚህም ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱን አክለዋል፡፡

ያለፉት ሁለት ዓመታት ለኢትዮጵያ ትልቅ የፈተና ጊዜ እንደነበሩ የገለጹት አቶ ደመቀ፣ መንግሥት ምንም እንኳ በመጀመሪያው የጦርነት ወቅት አገሪቱ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ተበልጣ የነበረ ቢሆንም፣ በሁለተኛው ዙር በነበረው ጦርነት ግን መንግሥት ጉዳዩን በተመለከተ የማለዘብና የማስገንዘብ የዲፐሎማሲ ሥራ በመከናወኑ የውጭ ጫና ማርገብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ፣ ‹‹ዕዳችንና የቤት ሥራችን አላለቀም፣ ኢትዮጵያ አሁንም የቀጠሉና እያኮበከቡ ያሉ አጀንዳዎች በተለይም ከሰብዓዊ መብት፣ ከታላቁ ህዳሴ ግድብና መሰል አዳዲስ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ጫናዎች እየመጡባት ነው፤›› ያሉት አቶ ደመቀ፣ ‹‹በቀጣይ የሚዘጋ ሒሳብ ባለመኖሩ ለዚሁ የሚመጥን ሠልፈኛ ያስፈልገናል፤›› ብለዋል፡፡

የአራት ዓመት የውጭ ተልዕኳቸውን አጠናቀው ወደ አገር ቤት የተመለሱ ዲፕሎማቶች ወደፊት የተለያዩ ሥምሪቶች እንደሚሰጣቸው የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በተጀመረው ሥልጠና ማጠናቀቂያ፣ ለአዳዲስ ዲፕሎማቶች የውጭ ሥምሪት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለበት የመካከለኛ ዘመን ዲፕሎማቶች እጥረት የተነሳ የረዥም ዘመን አገልግሎት ያላቸውን ዲፕሎማቶች በአግባቡ መጠቀም እንዴት አለብን የሚለውን በመገምገም ጠንካራ ሥራ እንደሚከናወን የተናገሩት አቶ ደመቀ፣ ‹‹ከዚህ በኋላ ሹልክ እያሉ መበተን አይኖርም፤›› ብለዋል፡፡

ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከወከሏቸው አገሮች ተልዕኮቸውን አጠናቀው የመጡትን ዲፕሎማቶች ሌላ የተለየ ኃላፊነት ለመስጠት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጋር ንግግር መጀመሩን ጠቁመዋል፡

በአፍሪካ ሊደርሺፕ አካዳሚ ለሁለት ሳምንታት ያህል በሚቆየው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማና ሥልጠና፣ እ.ኤ.አ. በ2023 የዲፕሎማሲ አግባብ ምን መምሰል እንዳለበት በመነጋገር አቅጣጫ እንደሚሰጥ አቶ ደመቀ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...