Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጤና ሚኒስቴር ለኩላሊት ንቅለ ተከላ አንድ መቶ ማሽኖችን ለመግዛት የገባውን ቃል አለመፈጸሙ...

ጤና ሚኒስቴር ለኩላሊት ንቅለ ተከላ አንድ መቶ ማሽኖችን ለመግዛት የገባውን ቃል አለመፈጸሙ ቅሬታ አስነሳ

ቀን:

  • ጤና ሚኒስቴር ቃል አለመግባቱን ገልጿል

በኢዮብ ትኩዬ

የጤና ሚኒስቴር ለኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና አገልግሎት የሚሆኑ 100 ማሽኖችን ለመግዛት ቃል ቢገባም፣ ማሽኖቹ ሳይገዙ ከአንድ ዓመት በላይ ማስቆጠራቸው ቅሬታ እንዳሳደረበት የኩላሊት ሕሙማን በጎ አድራጎት ማኅበር ገለጸ፡፡

ማሽኖቹ በጤና ሚኒስቴር አማካይነት እንደሚገዙ ከዚህ በፊት ቃል ተገብቶላቸው ባለመፈጸሙ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው፣ የኩላሊት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የኩላሊት ሕሙማን በሳምንት ሦስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት (ዳይሌሲስ) እንደሚያደርጉና ለከፍተኛ ወጪ እንደሚዳረጉ፣ ማኅበሩ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ ነበር ብለዋል፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማሽን እንደሚያስፈልግ ሲያሳስብ የነበረው ማኅበሩ፣ ከዚህ በፊት የጤና ሚኒስቴር 100 ማሽኖች እንደሚገዛ ቃል ቢገባም አለመገዛቱ ችግር ይቀረፋል የሚለውን ተስፋ እንዳከሸፈው አስታውቋል፡፡

ምንም እንኳ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ የሚረዱ 30 ማሽኖች ተገዝተው አገልግሎት እየሰጡ ቢሆንም፣ በተባለው መሠረት ተጨማሪ 100 ማሽኖች ቢገዙ ኖሮ ሕሙማን ለኩላሊት እጥበት የሚያወጡትን ወጪ ማስቀረት ይቻል እንደነበር አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡

የኩላሊት ሕሙማን አንድ ጊዜ የኩላሊት እጥበት ለማድረግ ሦስት ሺሕ ብር የሚጠየቁ ሲሆን፣ በሳምንት ሦስት ጊዜ እጥበት ለማድረግ ግድ የሚላቸው ሕሙማን ደግሞ ከሌሎች መድኃኒቶች ጋር በወር ከ30 ሺሕ ብር በላይ እንደሚያወጡ በተደጋጋሚ ይገለጻል፡፡

ከኩላሊት ሕሙማን በጎ አድራጎት ድርጅት በተገኘው መረጃ መሠረት፣ በኮቪድ-19 ምክንያት የኩላሊት ንቅለ ተከላ አገልግሎት ተቋርጦ በመቆየቱ ሕሙማኑን ለከፍተኛ ወጪ እየዳረገ መሆኑን ያስረዳል፡፡

ይሁን እንጂ በቅርቡ አገልግሎቱ በመጀመሩ ሕሙማኑ የተሻለ አገልግሎት እያገኙ ቢሆንም፣ አሁንም ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል፡፡

የጤና ሚኒስቴር 100 ማሽኖችን እገዛለሁ ብሎ ቃል ቢገባም አልገዛም የተባለውን ቅሬታ በተመለከተ፣ በጤና ሚኒስቴር በኩል ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉት አባስ ሐሰን (ዶ/ር) ቃል አለመገባቱን ነው ምላሽ የሰጡት፡፡

በአንድ ወቅት ማሽኖችን ያስገቡ ድርጅቶች መኖራቸውን ጠቁመው፣ ይሁን እንጂ የጤና ሚኒስቴር ቃል ተገብቷል ሲባል እንዳልሰሙና ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ምላሽ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡  

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ከግል ተቋማት መካከል የኩላሉት ንቅለ ተከላ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ያሉ ቢኖሩም፣ በጤና ሚኒስቴር በኩል ፈቃድ ባለመሰጠቱ መጀመር አለመቻላቸው ይነገራል፡፡

በኢትዮጵያ በግል ተቋማት ደረጃ የኩላሊትን ንቅለ ተከላ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የጤና ሚኒስቴርን ፈቃድ እየጠበቀ ያለው፣ ሊያና ሔልዝ ኬር የተሰኘው ተቋም ተጠቃሽ ነው፡፡

በግል ተቋማት ደረጃ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ ዝግጅቱን ቢጨርስም፣ ከጤና ሚኒስቴር ፈቃድ ባለመገኘቱ አገልግሎቱን መጀመር እንዳልተቻለ የሊያና ሔልዝ ኬር ኃላፊ ግርማ አባቢ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

አገልግሎቱን በግል ተቋማት ደረጃ ለመስጠት በጤና ሚኒስቴር የሚሰጠው ፈቃድ፣ በሕዝብ በተወካዮች ምክር ቤት መፅደቅ ስላለበት መጀመር አልተቻለም ብለዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር በኩልም በጉዳይ ላይ የሕግ ማዕቀፍ ባለመውጣቱ ጥያቄ እንዳቀረቡ ግርማ (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡ አክለውም በሊያና ሔልዝ ኬር በኩል ያለውን ሒደት በማጠናቀቅ ላይ እንደሆኑና ፈቃዱን ካገኙ በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡

ሊያና ሔልዝ ኬር በኢትዮጵያ በግል ተቋም ደረጃ ለመጀመርያ ጊዜ የኩላሊትን ንቅለ ተከላ ለመስጠት በሒደት ላይ ያለ ተቋም ነው፡፡

የኩላሊት ሕሙማን ንቅለ ተከላ ለማድረግ አቅም ስለማይፈቅድላቸውና የማሽን እጥረት በመኖሩ፣ በሳምንት ሦስት ጊዜ ለኩላሊት እጥበት ከፍተኛ ወጪ እንደሚጠየቁ ይናገራሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...