የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን ወደ መቀሌ የሚደረግ መደበኛ በረራ ከ ነገ ታሕሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡
ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ የአየር ትራንስፖርት በነገው ዕለት ይጀምራል ፡፡
በፌዴራል መንግስቱና በህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የአቬየሽን ሰራተኞች ወደ መቀሌ አቅንተው የመቀሌ አየር መንገድ ለበረራ ምቹ ሁኔታ ላይ መሆኑ እንደተረጋገጠ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ተናገረዋል፡፡
በረራው በቀን አንድ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ፥ የደንበኞቹ ፍላጎትን መሰረት በማድረግም የበረራው ቁጥሩ ከፍ ሊል የሚችልበትን ሁኔታ እንደሚፈጠርም ነው ዋና ስራ አሰፈጻሚው አክለዋል፡፡