በኳታር በተካሄደው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ለሦስተኛ ጊዜ ዋንጫ ያነሳችው አርጀንቲና በዕውቁ ተጫዋቿ ሊዮኔል ሜሲ ፎቶግራፍ ወይም የሚለብሰውን ማሊያ ቁጥር ‹‹10›› ለማተም አማራጭ መቅረቡ ተሰምቷል፡፡ ኢንዲያን ናሬቲቭ እንደሚለው፣ የአርጀንቲና ማዕከላዊ ባንክ በአገሪቱ የ1000 ፔሶ ኖት ላይ የሜሲን ምስል የማስቀመጥ ሐሳብ ሲሰነዝር፣ ባለሥልጣናት ደግሞ ‹‹10›› ቁጥርንና የቡድኑን አሠልጣኝ ስም ሊዮኔል ስካሎኒ ማስቀመጥ ይሻላል የሚል ሐሳብ ሰንዝረዋል፡፡ የትኛው አማራጭ ፀንቶ በ1000 ፔሶ ኖት ላይ ይሰፍር ይሆን?