Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለቻን ውድድር ዝግጅት መንግሥት 50 ሚሊዮን ብር እንዲሰጠው...

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለቻን ውድድር ዝግጅት መንግሥት 50 ሚሊዮን ብር እንዲሰጠው ጠየቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአልጄሪያ ለሚካሄደው የአፍሪካ አገሮች ሻምፒዮና (ቻን) ብሔራዊ ቡድን ለማዘጋጀት መንግሥት የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንዲያደርግለት ጠየቀ፡፡

ከጥር 5 እስከ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚካሄደው የቻን ውድድር ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ የመንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ያሳወቀ ሲሆን የመንግሥትን ምላሽ እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡

በምድብ አንድ ከአስተናጋጇ አልጄሪያ፣ ሞዛምቢክና ሊቢያ ጋር የተደለደለው የዋሊያዎቹ ስብስብ ሊጉ ታኅሣሥ 17 ቀን ከተቋረጠ በኋላ ወደ መደበኛ ልምምዱ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሠረት ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለብሔራዊ ቡድን እያደረገ ከሚገኘው አስተዳደራዊ ድጋፍ ጎን ለጎን ለቅድመ ዝግጅትና ከውድድር ጋር ተያያዥ ለሆኑ ወጪዎች ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም የሚያስፈልግ በመሆኑ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡን በማኅበራዊ ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

እንደ ፌዴሬሽኑ ማብራሪያ ከሆነ ከመንግሥት ድጋፍ በተጨማሪ የተለያዩ የገቢ አማራጮችን እየተመለከተና አጋር ተቋማትን እያፈላለገ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ከሳምንታት በፊት ለ42 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገው የነበሩት የዋሊያዎቹ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ፣ በድሬዳዋ እየተካሄደ በሚገኘው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ ተገኝተው የተጫዋቾችን ወቅታዊ ብቃትና ሁኔታ በመገምገም የተጫዋቾችን ቁጥር ወደ 28 በመቀነስ ጥሪ አድርገዋል፡፡

የተጠሩት ተጫዋቾች ከታኅሣሥ 18 ጀምሮ በጽሕፈት ቤት ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ያሳሰበው ፌዴሬሽኑ በማግስቱ የጤናና የአካል ብቃት ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ልምምድ ይጀምራሉ ብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...