Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጎዳና የወጡ ዜጎችን ሕይወት ይታደጋል የተባለለት ረቂቅ አዋጅ ለዓመታት አለመፅደቁ ጥያቄ አስነሳ

ጎዳና የወጡ ዜጎችን ሕይወት ይታደጋል የተባለለት ረቂቅ አዋጅ ለዓመታት አለመፅደቁ ጥያቄ አስነሳ

ቀን:

ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎችን የማኅበራዊ አገልግሎት በመስጠት እንዲቋቋሙ ለማድረግ ይረዳል የተባለለት ብሔራዊ የማኅበራዊ ጥበቃ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ለረዥም ዓመታት መዘግየት፣ አግባብ እንዳልሆነ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ አቀረቡ፡፡

ረቂቁ አዋጁ ከተዘጋጀ አራት ዓመታት ቢሆነውም፣ ፀድቆ ወደ ሥራ መግባት አለመቻሉን በመጥቀስ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ትኩረት እንዳልሰጠው ማሳያ ነው ሲሉ፣ የመንግሥት ወጭ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተናግረዋል፡፡

ረቂቁ ከተዘጋጀ በኋላ ፀድቆ ወደ ሥራ መግባት ሲገባው ይህን ያህል ጊዜ መቆየቱ ተገቢነት የሌለው በመሆኑ፣ አፋጣኝ ምላሽ ሊያገኝ እንደሚገባ፣ ወ/ሮ እየሩሳሌም ሌዊ የተባሉ የምክር ቤት አባል ጠይቀዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የአዋጁ መዘግየትን በሚመለት የተጠየቀው፣ ቋሚ ኮሚቴው የሴቶችና ማኅበራዊ ጉደይ ሚኒስቴር ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ እናቶች፣ ከሕፃን ልጆቻቸው ጋር መልሶ ለማቋቋም የተዘረጋውን አሠራር በተመለከተ የተደረገ የክዋኔ ኦዲት ላይ ሐሙስ ታኅሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት በተደረገበት ወቅተ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ይህ ረቂቅ አዋጅ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በዝግጅት ላይ እንዳለ ቢነገርም፣ ፀድቆ ወደ ሥራ እንዳልገባ በመግለጽ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ቋሚ ኮሚቴው ዕገዛ አድርጎበት እንዲፀድቅ ጠይቀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ አዋጁ እንዲፀድቅ ከካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ጋር በመሆን ክትትል መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ጎዳና ላይ ለወጡ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ፣ ከውጭ አገር በሚገኝ ገቢ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ እንዳይሆን የሚረዳ መሆኑን፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

በረቂቅ ደረጃ የሚገኘው ይህ ሕግ ከፀደቀ ከባለሀብቶች፣ ከንግዱ ማኅበረሰብና ከዜጎች ሀብት ለማሰባሰብ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ ወደ ሥራ ሲገባ ማኅበራዊ ኃላፊነትን በተለይ የግሉ ዘርፍ በዘፈቀደ ሳይሆን፣ በተዘረጋ ሲስተም ከሚያገኘው ትርፍ ላይ የተወሰነ ፐርሰንት እየተቆረጠ ወደ ፈንዱ እንዲገባ የሚደረግበት አሠራርን የያዘ ነው፡፡

ሚኒስትሯ አዋጁ ፀድቆ በሥራ ላይ ቢውል ዜጎች ለባሰ ችግር ሳይጋለጡና ወደ ሜዳ ሳይወጡ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያግዝ በመሆኑ፣ ፓርላማው ዕገዛ ያድርግልን፤›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ አዋጁ ሊፀድቅ ያልቻለው አገሪቱ ባለፉት ዓመታት ካሳለፈቻቸው አስቸጋሪ ጊዜያት ጋር ተዳምሮ፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሌሎች ረቂቅ አዋጆች ጋር ወረፋ በመጠበቅ ላይ በመሆኑ ጭምር እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...