Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች አከፋፋዮችንና ቸርቻሪዎችን የመምረጥ መብት ተሰጣቸው

ሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች አከፋፋዮችንና ቸርቻሪዎችን የመምረጥ መብት ተሰጣቸው

ቀን:

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ታኅሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ በሚያደርገው አዲስ የሲሚንቶ አቅርቦትና ሥርጭት መመርያ፣ የሲሚንቶ አምራቾች የምርታቸውን አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎችን በራሳቸው የመምረጥ መብት እንዲኖራቸው ተደረገ፡፡

ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ሚኒስቴሩ አውጥቶት በነበረው መመርያ ከፋብሪካ አውጥተው በየክልሉ የሚያከፋፍሉ የመንግሥትና የማኅበር ድርጅቶች ተመርጠው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ባሻሻለው መመርያ ግን የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ‹‹በቁጥጥርና በክትትል ብቻ ይሆናል›› ሲሉ ሚኒስቴር ዴኤታው አቶ ተሻለ በልሁ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

እንደ ሚኒስቴር ዴኤታው ገለጻ፣ በዚህ መመርያ ከተከለከሉ ጉዳዮች አንደኛው ሲሚንቶን በየመንገዱ በክትትልና ቁጥጥር ምክንያት ማድረግ ሲሆን፣ ተቆጣጣሪ አካላቶች ይህን በሚመለከት የተሰጣቸው ኃላፊነት መነሳቱን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የፋብራካ ዋጋን በሚመለከት መንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አሁንም ለተወሰነ ጊዜ ዋጋን እያወጣ እንደሚቀጥልና፣ በየስድስት ወሩ ይህንን እየከለሰ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡ ባለፈው መስከረም ወር የፋብራካን ዋጋ አውጥቶ የነበረ ሲሆን፣ በአምራቾች በኩል ዋጋ አወጣጡ ቅሬታን ሲያስነሳ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መመርያውን ለመቀየር ካስገደዱትና ‹‹የበፊቱ መመርያ ተግዳሮቶች›› ብለው ሚኒስቴር ዴኤታው ሲገልጹ፣ የፋብሪካዎች የማምረትና የማቅረብ ችግር፣ የአቅርቦትና ፍላጎት በአከፋፋዮች ምክንያት አለመጣጣም፣ እንዲሁም የቸርቻሪዎች ከፍተኛ የትርፍ መጠን መውሰድ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የፋብራካዎችን የማምረት አቅም በማሳደግ በኩል ከዚህ መመርያ ጋር የተሰጠ የቤት ሥራ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ተሻለ፣ የማዕድን ሚኒስቴር በዚህ በኩል አብሮ እየሠራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አዲሱና ለስድስት ወራት በገበያ ላይ የሚውለው የፋብሪካ ዋጋ፣ መስከረም ላይ ወጥቶ ከነበረው ለፋብሪካዎች የተወሰነ ዋጋ ጭማሪ ተደርጎላቸዋል፡፡ አሥራ አንድ ፋብሪካዎች በአማካይ ሲሸጡበት የነበረው ዋጋ በኩንታል 590 ብር ሲሆን፣ አሁን የተሻሻለው ግን በኩንታል 758 ብር ተደርጓል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...