Friday, March 1, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ስልካቸውን አጥፍተው ለሦስት ቀናት ከቆዩበት ስብሰባ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ ባለቤታቸው ምን ዓይነት አሳሳቢ ጉዳይ ስልክ አዘግቶ እንደሰወራቸው ለማወቅ መጠየቅ ጀመሩ]

 • ፓርቲያችን ባቀረበው ሰነድ ላይ እየተወያየን ነበር።
 • የምን ሰነድ?
 • አቅምን በውጤት ፈተናን በስኬት የሚል ሰነድ ነው።
 • ታዲያ እንዴት ነበር ውይይቱ?
 • በስኬት ተጠናቋል፡፡
 • መቼም የዚህ አገር ችግርና ችግሩን ለመፍታት የሚደረግ ስብሰባ ማለቂያ የለውም።
 • እንዴት?
 • አንድ ችግር ሲመጣ እናንተ ችግሩን ለመፍታት ስትሰበሰቡ፣ ሌላ ችግር ሲመጣ እናንተ ስትሰበሰቡ …
 • እሺ …
 • የሰሜኑ ችግር ተቀረፈ ሲባል ይኸው በመሀል አገር ደግሞ የባንዲራና የመዝሙር ተቃውሞ ሲቀሰቀስ እናንተም ስትሰበሰቡ ….
 • እሺ…?
 • ይኸው …መከራና ስብሰባ እየተፈራረቁብን ጊዜያችንን ፈጀነው ማለቴ ነው።
 • አትሳሳቺ!
 • ምን ተሳሳትኩ?
 • እኛ ችግርና ፈተናን አንቺ እንደምታስቢው አንመለከታቸውም፣ ሥጋትም አይፈጥሩብንም።
 • ምንድነው ታዲያ የሚፈጥሩባችሁ?
 • ብርታት!
 • ምን አለ ደንዳና ልብ ሰጥቶን እንደናንተ በሆን!
 • አትሳሳቺ!
 • እንዴት?
 • ይህ አመለካከታችን ከድንዳኔ አይደለም የሚመነጨው።
 • እ…
 • ከትንታኔ ነው፡፡
 • ታዲያ ትንታኔያችሁ ለምን ሊፈታው አልቻለም?
 • ምኑን?
 • ችግርና ፈተናውን?
 • እንደነገርኩሽ ነው።
 • ምን?
 • የእኛ ትንታኔ ችግርና ፈተናዎችን ስለመፍታት አያተኩርም።
 • ታዲያ ምን ላይ ነው የሚያተኩረው?
 • ትንታኔያችን?
 • እህ…?
 • ፈተናዎችን ወደ ዕድል መቀየር፡፡
 • ከዚያስ?
 • ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማማ ማሸጋገር!
 • ብቻ እንዳይሰሟችሁ?
 • እነ ማን?
 • ማትሪክ ተፈታኞች፡፡
 • ትቀለጃለሽ አይደል?
 • ቀልዴን አይደለም። እንዲያውም ሕዝቡ ራሱ እዚህ ላይ ቢያተኩር ጥሩ ነበር።
 • ምን ላይ ቢያተኩር?
 • ፈታናውን ወደ ዕድል ስለመቀየር፡፡
 • ምንድነው የሕዝቡ ፈተና?
 • እናንተው!

[ክቡር ሚኒስትሩ በሰሞኑ የፓርቲ ስብሰባ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ የሚያሻግሩ ውሳኔዎች መወሰናቸውን ለሕዝብ እንዲያሳውቁ በተሰጣቸው ኃላፊነት መሠረት የሚያደርጉትን የንግግር ይዘት ከአማካሪያቸው ጋር ሆነው እያረቀቁ ነው]

 • ፈተናን ወደ ዕድል በመቀየር ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማማ ማሻገር የሚለው እንዳይቀር!
 • ክቡር ሚኒስትር እሱማ አይቀርም፣ ይካተታል ግን…?
 • ግን ምን?
 • ያው ሕዝቡ ካለበት ችግር አኳያ መጠየቁ አይቀርም።
 • ምን?
 • ፈታናዎቹ እንዴት ነው ወደ ዕድል የሚቀየሩት ማለቱ አይቀርም።
 • ንግግር እንጂ ውይይት እኮ አይኖርም።
 • ቢሆንም እንዴት የሚለውን መስማት ይፈልጋል።
 • ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?
 • ያልተለመዱ ሐሳቦችን ማንሳት ጥሩ ይመስለኛል።
 • ያልተለመዱ ማለት?
 • አሃ …የሚያስብል ካልሆነም ኮንፊውዝ ማድርግ የሚችል ሐሳብ ቢነሳ ተስፋ ወይም…
 • ወይም ጊዜ ይሰጣል።
 • እና ምን ቢነሳ ይሻላል?
 • ለምሳሌ የFive D ሞዴልን በመጠቀም ችግሮችን ወደ ዕድል ለመቀየር ይሠራል ማለት እንችላለን።
 • እሱ ባለፈው ተብሏል።
 • ተብሏል?
 • የሰማሁ መሰለኝ።
 • ከሆነ የ5ቱ መ ሕጎች ተግባራዊ እንዲደረጉ ተወስኗል ማለት እንችላለን፣ ምን ያስባሉ?
 • ሳይሻል አይቀርም፣ ግን ምንድናቸው የሚል ጥያቄ አይፈጥርም?
 • እንዘረዝራቸዋለን።
 • ጥሩ። ቀጥል…
 • የመጀመሪያው ‹‹መ›› መሥራት ነው።
 • እሺ …
 • ሁለተኛው ‹‹መ›› መለወጥ ነው።
 • ጥሩ ነው።
 • ሦስተኛው ‹‹መ›› … ሙስናን መታገል ነው።
 • ‹‹ሙ›› ገባሃ?
 • ምን አሉኝ?
 • ዘለልክ ወደ ‹‹መ›› ተመለስ?!
 • ኦ… ይቅርታ ምን ብንለው ይሻላል?
 • ‹‹መ›› መስረቅን መታገል፣ አይሆንም?
 • በጣም ጥሩ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • በል እየተጠነቀቅክ?
 • ለምን?
 • ከ 5 እንዳናልፍ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...

የጋራ ድላችን!

ከፒያሳ ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። ለበርካታ ደቂቃዎች ሠልፍ ይዘን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ ነው የሚደንቀው? የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ሕዝባዊ ውይይት ላይ ምን ጉዳዮች ተነሱ? በአስማት ነው የምንኖረው ሲሉ ቅሬታቸውን...

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...