Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምሩሲያና ቻይና እያጠናከሩ የመጡት የጋራ የጦር ልምምድ

ሩሲያና ቻይና እያጠናከሩ የመጡት የጋራ የጦር ልምምድ

ቀን:

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ በሚቀርቡ በርካታ አጀንዳዎች ተመሳሳይ አቋም በማራመድ ከምዕራባውያኑ በተቃራኒ በመቆም የሚታወቁት ሩሲያና ቻይና፣ ዛሬ ታኅሣሥ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የጀመሩትንና ለሳምንት ይቆያል የተባለውን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ይፋ አድርገዋል፡፡

የቻይና መንግሥትን ጠቅሶ አልጄዚራ እንደዘገበው፣ የቻይናና የሩሲያ ባህር ኃይል የጋራ የጦር ልምምድ የተጀመረው በምሥራቅ ቻይና ባህር ላይ ሲሆን፣ በጋራ የሚያደርጉትን ወታደራዊ ልምምድም እያጠናከሩ ይገኛሉ፡፡

እ.ኤ.አ. በ2021 መገባደጃ 10 ሺሕ የምድርና የአየር ኃይል ጦር አባላት የተሳተፉበት የጋራ የጦር ልምምድ ያደረጉት አገሮቹ፣ እ.ኤ.አ. ከ2005 ወዲህ ለሩሲያ ወታደሮች የቻይና የጦር መሣሪያዎችን ለመጠቀም ዕድል የፈጠረ እንደነበርም ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የሩሲያና የቻይና የጋራ ጦር ልምምድ በምዕራባውያኑ ዘንድ ያለው ዕይታ አሉታዊ ቢሆንም፣ የሁለቱ አገሮች ትብብር የሚገለጽበት፣ እምነት የሚገነባበትና ስትራቴጂያዊ ትብብራቸው የሚያድግበት ተደርጎ በሁለቱ አገሮች ይወሰዳል፡፡

የባህር ላይ ደኅንነት ሥጋትን በብቃት ለመመለስና የሩሲያና ቻይና ስትራቴጂያዊ ትብብርን ይበልጥ ለማጠናከር ያስችላል በተባለው የአሁኑ ወታደራዊ ልምምድ፣ የጦር መርከቦች የሚሳተፉበት መሆኑንም የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህ ልምምድ የቻይና ባህር ኃይል በርካታ የውኃ ላይና ሰርጓጅ የጦር መርከቦችን ጥቅም ላይ የሚያውል ሲሆን፣ የሁለቱ ወገኖች የጦር ጀቶችም የጋራ ልምምድ ያደርጋሉ፡፡ የጋራ የጦር ልምምድ ከማድረግ ጎን ለጎንም የሩሲያና የቻይና እርስ በርስ እየተጋገዙና የፖለቲካ ሽፋን እየተሰጣጡ ይገኛሉ፡፡

በተለይ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በገባችበት ጦርነት ዙሪያ ከምዕራባውያኑ ለሚደርስባት ጫና ቻይና ከጎኗ ስትሆን፣ በቻይናና በታይዋን መካከል ያለውን አለመግባባት ተመሥርቶ አሜሪካ ለታይዋን የምታደርገውን ድጋፍ ደግሞ ሩሲያ ከቻይና ጎን ቆማ ትቃወማለች፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ፣ ቻይናና ሩሲያ በመካከላቸው ያሉ ልዩነቶችን ወደጎን በመተው የጋራ ጦር ልምምዳቸውን ማጠናከራቸው፣ ደግሞ አሜሪካ መራሹ የምዕራባውያን የፖለቲካ ሥርዓትን ለመቃወም ነው አስብሏቸዋል፡፡

ለምዕራባውያን ሥጋት የሆነው የቻይናና ሩሲያ ትብብር በየአቅጣጫው የሚገለጽም ሆኗል፡፡

ምዕራባውያን፣ ሩሲያ ዩክሬንን ወራለች ብለው ማዕቀብ ሲጥሉ፣ ቻይና ምዕራባውያንን በመቃወም አጋርነቱን ከመግለጽ ባለፈም፡፡ አሜሪካና የሰሜን ጦር ቃል ኪደን ድርጅት (ኔቶ) የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ለፀብ አጫሪነት እያነሳሱ ነው ስትል ከርማለች፡፡

ቻይና የምዕራባውያኑን ማዕቀብ ከማጣጣል ባለፈም ከሩሲያ ነዳጅ ዘይትና ጋዝ በብዛት ትገዛለች፡፡

በኔቶ የአሜሪካ አምባሳደር ጁሊያን ስሚዝ ለፋይናንሻል ታይምስ እንደሚሉትም፣ የሩሲያና ቻይና ትብብር የኔቶን እሴት ያጣጣል ነው፡፡ በመሆኑም የኔቶ ጥምረት ይህንን ጉዳዬ ብሎ ሊያየው ይገባል፡፡

ቻይናና ሩሲያ የትራንስአትላንቲክ ትብብርን ለመከፋፈል እየሠሩ ነው፡፡ የሚሉት ስሚዝ፣ ጉዳዩን ማየት ይገባል ብለዋል፡፡

ኔቶ፣ ‹‹ቻይና የኔቶ ስትራቴጂያዊ ተግዳሮት ናት›› ሲል በሰኔ 2022 ላይ በዝርዝሩ አስፍሯል፡፡ ቻይናን የምዕራባውያን የጦር ትብብር፣ ፍላጎት፣ ደኅንነትና እሴት አታከብርም ይላታል፡፡

ኔቶም ሆነ ምዕራባውያን አገሮች ከቻይናና ሩሲያ ጋር ያላቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ወታደራዊ ፉክክር የዓለም ኃያላንን በሁለት ጎራ ከፍሏል፡፡

አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ተደጋጋሚ የጦር ልምምድ ስታደርግ፣ ቻይና ደግሞ ከሩሲያ ጋር ታደርጋለች፡፡ የአሜሪካና የደቡብ ኮሪያ የጦር ልምምድ በሚደረግባቸው ወቅቶች ሰሜን ኮሪያ የተወንጫፊ ሚሳይል ሙከራ በማድረግ አፀፋ የምትሰጥ ቢሆንም፣ ይህን ሩሲያና ቻይና የጦር ልምምድ በሚያደርጉ ጊዜ አታደርገውም፡፡ ሆኖም ጃፓንና ሌሎች የቀጣናው አገሮች ሥጋታቸውን ይገልጻሉ፡፡

ባለፈው ወር የሩሲያ አየር ኃይልና የቻይና ቦምብ ጣይ ጀቶች በጃፓን ባህርና በምሥራቅ ቻይና ባህር ላይ ማለፋቸው ይታወሳል፡፡ በመስከረም ቻይና 2,000 ወታደሮች፣ ከ300 በላይ የጦር ተሽከርካሪዎች 21 ተዋጊ ጀቶች እንዲሁም ሦስት የጦር መርከቦች የተሳተፉበት የጋራ የጦር ልምምዷን ከሩሲያ ጋር አድርጋለች፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...