Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በቂ ምክክር ሳይደረግበት ወደ ትግበራ እንዳይገባ ተመድና ኢሰመኮ ጠየቁ

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በቂ ምክክር ሳይደረግበት ወደ ትግበራ እንዳይገባ ተመድና ኢሰመኮ ጠየቁ

ቀን:

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋር በጋራ ባወጡት ምክረ ሐሳብ፣ በኢትዮጵያ የተጀመረው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ከኅብረተሰቡ ጋር በቂ ምክክር ሳይደረግበት ወደ ትግበራ እንዳይገባ ጠየቁ፡፡

ሁለቱ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ማክሰኞ ታኅሳስ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ባደረጉት ባለሰባት ገጽ ምክረ ሐሳብ በፌደራል መንግሥቱና በሕወሓት መካከል የተካሄደውን የሰላም ስምምነት እንደሚያደንቁ ጠቅሰው፣ በመንግሥት እየተዘጋጀ ያለው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች ሳይካተቱበት ወደ ውሳኔ እንዳያመራ አሳስበዋል፡፡

ለኢትዮጵያ መንግሥት፣ በሰላም ድርድሩ ላይ ለሚሠሩ አካላት፣ እንዲሁም በሽግግር ፖሊሲው ላይ ለሚንቀሳቀሱ የአገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ይፋ የተደረገ ምክረ ሐሳብ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ባለፈው 2014 ዓ.ም. የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመሆን፣ በትግራይ ክልል ከተካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ላይ ምርመራ አካሂደው ውጤቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ከተመላከቱ ምክረ ሐሳቦች መካከል፣ የሽግግር ፍትሕ እንዲጀመር የሚል እንደነበር ምክትል ኮሚሽነሯ አስታውሰዋል፡፡

በዚህም መሠረት አዲሱ ምክረ ሐሳብ በዝግጅት ላይ ያለውን የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት፣ በተለይም የተጎጂ ማኅበረሰብ ክፍሎች፣ የሲቪክ ማኅበራትና ፖሊሲ አውጪዎች ምክክርና ውይይት እንዲያቀርቡበት በሚል ዕሳቤ የተዘጋጀ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሯ አክለው ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት እውነተኛ፣ አሳታፊ፣ ሁሉን አቀፍ፣ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታዎችን ማዕከል ያደረገና ዘላቂ የሽግግር ፍትሕን ማምጣትን ዓላማው ያደረገ ውይይት ከሐምሌ 2014 ዓ.ም. እስከ ታኅሳስ 2015 ዓ.ም. ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉትን ጨምሮ በአማራ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌ፣ በሐረሪ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር መካሄዱን አስታውቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ በነሐሴ 2014 ዓ.ም. በትግራይ ክልል ይደረጋል ተብሎ ታስቦ የነበረው ውይይት በወቅቱ በነበረው ጦርነት ምክንያት ባይካሄድም፣ በቀጣይ በትግራይ ክልል ያለው የሰላም ሁኔታ ሲስተካከል በዚሁ ክልልና በሌሎች ክልሎች ውይይቱ እንደሚካሄድ በምክረ ሐሳቡ ላይ ቀርቧል፡፡ በምክረ ሐሳቡ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረውን የሽግግር ፍትሕ ሥርዓት አካባቢያዊና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሁለቱ አካላት ከኅብረተሰቡ ጋር ባደረጉዋቸው 13 የመስክ ውይይቶች የተነሱት ቁልፍና የመጀመሪያ ደረጃ ሥጋቶች የሰላምና ፀጥታ፣ የካሳ ክፍያ፣ እውነታን ማረጋገጥና ዕውቅና መስጠት፣ ይቅርታ አደራረግ፣ ተጠያቂነት፣ ግጭቶች በድጋሚ ላለመከሰታቸው ማረጋገጫ፣ እንዲሁም ትርጉም ያለው ተሳትፎና በመጨረሻ ግምገማ ተደርጎበት አፈጻጸሙ የሚለካበት መንገድ እንዲኖር የሚሉት ተጠቅሰዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት ባወጡት ምክረ ሐሳብ ዜጎች ጦርነቱ በድጋሚ የማይከሰት ስለመሆኑ ማረጋገጫ የሌላቸው መሆኑን በመግለጽ፣ የሰላምና የፀጥታው ሁኔታ አሁንም ሥጋት ውስጥ ጥሏቸዋል ተብሏል፡፡ 

በመሆኑም የታሰበው የሽግግር ፍትሕ አፈጻጸም ቀጣናዊ፣ አኅጉራዊ፣ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያላቸውን መርሆዎችና የሰብዓዊ መብት ሕጎችን፣ እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች የተገኙ ልምዶችን በመዳሰስና በማየት እንዲከናወን ጠይቀዋል፡፡

በተጨማም የኢትዮጵያን የፖለቲካ፣ የተቋማዊ፣ የሕግ፣ የታሪክ፣ የባህል፣ እንዲሁም ተጎጂዎች የሚያቀርቡትንና የሚጠብቋቸውን ጉዳዮች ከዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር በማጣጣም እንዲሆን ተጠይቋል፡፡

በሽግግሩ ፍትሕ ክንውን ውስጥ ወደኋላ ከመመልከት ይልቅ ወደፊት ማኅበረሰባዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ተስፋዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ በተለይም በነበረው ጦርነት የተከሰቱ የመብት ጥሰቶችን፣ ትልልቅ የሕግ ግድፈቶችን፣ ፍትሐዊ ያልሆነ የሥልጣን ክፍፍልን፣ አድልኦና መገለልን፣ ተቋማዊ እጥረቶችን፣ መዋቅራዊ እምቢተኝነትን፣ እንዲሁም መሰል የአገሪቱን ሰላምና ደኅንነት አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ጉዳዮችን ሊፈታ በሚችል መንገድ እንዲከናወን ሁለቱ ተቋማት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...