Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአማራ ክልል የገጠር መሬትን በስጦታ ማስተላለፍ ለጊዜው ታገደ

በአማራ ክልል የገጠር መሬትን በስጦታ ማስተላለፍ ለጊዜው ታገደ

ቀን:

የአማራ ክልል መሬት ቢሮ በከተሞች ዙሪያ ገጠር አካባቢዎች በከተማ የአስተዳደር ፕላን ወሰን በተጠቃለለ የእርሻ መሬቶች ላይ ሕገወጥነት በመበራከቱ፣ በስጦታና መሰል ተግባራት የሚደረግ የመሬት ማስተላለፍ አገልግሎትን በጊዜያዊነት አገደ፡፡

ቢሮው ባደረገው ክትትልና ግምገማ በከተሞች ዙሪያ ያለ የገጠር መሬት አገልግሎት ተግባራት፣ ለከፍተኛ ብክነትና የአስተዳደር ብልሽት እየተጋለጠ መሆኑ በግልጽ እንደተደረሰበት አስታውቋል፡፡

ድርጊቱ የከተሞች መስፋፋትና የኢንዱስትሪ ልማትን የሚገታ፣ እንዲሁም መሬትን በቁጠባ የመጠቀምና ብክነትን የመከላከል ዘላቂ የሆነ የአርሶ አደር ባለይዞታ ጥቅምን አስከብሮ በመሄድ በኩል፣ በክልሉ ከፍተኛ ችግር በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ፣ በመሬት ቢሮ ኃላፊው አቶ ሲሳይ ዳምጤ ተፈርሞ ለሁሉም ዞኖችና ለሪጆፖሊ መሬት መምርያዎች የተላለፈው ሰርኩላር ያስረዳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በጥናት ላይ ተመሥርቶ ግልጽ የሆነ አሠራር እስኪወርድ ድረስ ማንኛውም ከገጠር መሬት ስጦታ ጋር የተያያዘ አገልግሎትን ቢሮው ማገዱን ገልጾ፣ የዞን መምርያዎች በሥራቸው ላሉ የገጠር ወረዳ መሬት ጽሕፈት ቤቶች የተላከላቸውን ሰርኩላር መነሻ በማድረግ ተግባራዊ እንዲደረጉ በጥብቅ አሳስቧል፡፡

በክልሉ ባሉ የገጠር መሬት ይዞታ ባለባቸው የገጠርና ከተማ አስተዳደሮች የገጠር መሬትን አገልግሎት የማሻሻል ሥራ በመከናወን ላይ ቢገኝም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ 252/09 አንቀጽ 16 እና እሱን ተከትሎ በወጣው ደንብና መመርያ መሠረት በከተሞች ዙሪያ ያለን የገጠር መሬት ከአዋጁ፣ ከደንብና ከመመርያ ውጪ ሕጉን በተዛባ መንገድ በመተርጎም በመፈጸም በኩል ከፍተኛ የሆነ ችግር እየገጠመ ነው ብሏል፡፡

ከአማራ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009 ዓ.ም. አንቀጽ 16 ላይ እንደተገለጸው፣ ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ የይዞታም ሆነ የመጠቀም መብቱን በክልሉ ውስጥ ለሚኖርና በአዋጁ ላይ ከተመለከቱ መመዘኛዎች መካከል ቢያንስ አንዱን ለሚያሟላ ሰው በስጦታ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡

ማንኛውም የገጠር መሬት ባለ ይዞታ፣ ‹‹በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በዚሁ ሙያ መተዳደር ለሚፈልግ ልጁ ወይም የልጅ ልጁ ወይም ለማንኛውም ሌላ የቤተሰቡ አባል›› አንደኛው በስጦታ የሚተላለፍበት መመዘኛ ሲሆን፣ ‹‹መረጃውን በጽሑፍ አረጋግጦ እስከሰጠ ድረስ በወቅቱ እየጦረው ላለና አገልግሎኛል ወይም እያገለገለኝ ነው ብሎ ላመነውና በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በዚሁ ሙያ መተዳደር ለሚፈልግ ሌላ ማንኛውም ሰው››፣ ሌላው የገጠር መሬት በስጦታ ለማስተላለፍ መመዘኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የአማራ ክልል መሬት ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ከታኅሳስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለተላለፈው ደብዳቤ መሻሪያ እስካልደረሰ ድረስ የተሰጠ አገልግሎት በተቋማዊ አሠራር ሕጋዊ ተቀባይነት የለውም፡፡ ሰርኩላሩን ተላልፈው በሕገወጥ ድርጊት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የሆኑ ተቋማትና ባለሙያዎች በሕግ የሚያስጠይቃቸው መሆኑን አሳስቧል፡፡

ሪፖርተር በአማራ ክልል ከገጠር መሬት ስጦታ ጋር ተያይዞ ስለታገደው አገልግሎት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ ወደ አማራ ክልል መሬት ቢሮ በተደጋጋሚ ላደረገው የስልክ ጥሪ ምላሽ ማግኘት አልቻለም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...