Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊተስፋ የተጣለበት የፈጠራ ሥራዎችን መሬት ላይ የማውረድ ሒደት

ተስፋ የተጣለበት የፈጠራ ሥራዎችን መሬት ላይ የማውረድ ሒደት

ቀን:

በአበበ ፍቅር

በየዓመቱ በርካታ ወጣቶች አዳዲስ የሥራ ፈጠራቸውን ይዘው ብቅ በማለት ለዕይታ ሲያቀርቡ ይስተዋላል፡፡ የፈጠራ ሥራዎችም የቴክኖሎጂ ቅይጥ በመሆናቸው፣ የማኅበረሰቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ያቃልላሉ ተብሎ ተስፋ ይጣልባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከተስፋ በዘለለ እስካሁን መሬት ላይ ጠብ ያለ ነገር እንደሌለና ወጣቶች ሥራቸው ድካም ብቻ እንደሆነባቸው ይናገራሉ፡፡

ጅምሩ የፈጠራ ሥራቸው ዳር ደርሶ ራሳቸውንና ማኅበረሰባቸውን ለመጥቀም እንዳይችሉ ዘርፈ ብዙ ትብታቦች ይዞ ያስቀራቸዋል፡፡ ሥራ ፈጣሪዎቹ እንደ ዋነኛ ችግር ብለው የሚያነሱት የገንዘብ እጥረትን ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሐሰን ሁሴንም ችግሩ መኖሩን አምነው ዋናው ችግር ግን የአስተሳሰብና የክህሎት መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ብዙ ወጣቶች ለችግሩ ኃላፊነት ወስደው መፍትሔና ሌሎች አማራጮችን ከመፈለግ ይልቅ፣ በአንድ ሐሳብ ተቸንክረው የፈጠራ ሥራቸውን ወደ ገንዘብ ከመቀየር ይልቅ ባለበት እንዲቆም ማድረጋቸውንም እንደ ችግር ያነሱታል፡፡

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ፣ በእንጥልጥል ላይ የሚቀረው የመንግሥት አሠራርም ችግር ነው፡፡ የፈጠራ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ከመንግሥት አሠራር ጀምሮ ለኢንተርፕርነርሽፕ ምቹ ያልሆነው ሥነ ምኅዳር መስተካከል ይኖርበታል፡፡

ኋላቀር የሆነው የመንግሥት አሠራርና ከላይ የተንጠለጠሉ ፖሊሲዎች መሬት ላይ ወርደው ወደ ተግባር ሲገቡ፣ ውስብስብ የሆኑ ሕጎችና ደንቦች ይበዙበት ነበር፡፡ መንግሥትም ይህንን ኋላቀር አሠራር ለመቀየር በተለይም በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ ምቹ የአሠራር መዋቅር በመፍጠር ረገድ ተስፋ አሳይቷል፡፡ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በዘጠኝ ሚኒስቴሮች ተበታትኖ የነበረውን አሠራር አሁን ላይ በተወሰነ መልኩ ወደ አንድ ተቋም በማጠቃለል የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት በመባል ራሱን ችሎ መደራጀቱና ዕውቅና ማግኘቱን አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል ለዘርፉ ዕድገት የገንዘብ አቅርቦት ትልቅ ሚና አለው፡፡ ይሁን እንጂ እስካሁን በነበረው አሠራር የፈጠራ ሥራቸውን ይዘው የሚመጡ ሰዎች፣ ቋሚ ገንዘብ እንደ ቤትና መኪና እንዲሁም የመሥሪያ ቦታ ከሌላቸው ከባንክ ለመበደር አይችሉም ነበር፡፡ በዚህም ብዙ ወጣቶች የፈጠራ ሥራቸውን ማሳደግና ለውጭ ገበያ ማቅረብ እየቻሉ በገንዘብ እጥረት ታስረው መቆየታቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ይናገራሉ፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታትም፣ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር አብረው እየሠሩና ልማት ባንክ በኢንርፕርነርሽፕ ታቅፈው የፈጠራ ሥራቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ያለ ምንም ማስያዣ እስከ አራት ቢሊዮን ብር ለማበደር ዘንድሮ ወደ ሥራ መግባቱን አክለዋል፡፡

የብድሩን አሰጣጥ ተግባራዊ ለማድረግም ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመሆን መመርያ ተዘጋጅቶ እንደሚሠራም አቶ ሁሴን አብራርተዋል፡፡

ከሌሎች ባንኮች ጋር ለመሥራት የተስማሙ ሲሆን፣ በቅርቡ አዋሽ ባንክ ‹‹ታታሪዎች›› በሚል የሐሳብ ውድድር አድርጎ ለአሸናፊዎች ከአንድ ሚሊዮን እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚደርስ ገንዘብ ያለ መያዣ ብድር ለመስጠት ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ዳሸን ባንክና ሌሎች ባንኮች ለሥራው ትኩረት ሰጥተው ለመሥራት እየተዘጋጁ እንደሆነና መንግሥትም ለሥራው ትኩረት እንደሰጠው  ተናግረዋል፡፡

እስካሁን በነበረው አሠራር ብዙ የፈጠራ ሥራዎች በየቦታው መደርደሪያ ላይ እንደቀሩ አንስተው፣ በተያዘው አሠራር ግን የሚሠሩ የፈጠራ ሥራዎች ወደ ገበያ እንዲደርሱ ከማድረግ ባሻገር ለፈጣሪዎች የገቢና የሀብት ምንጭ ለዜጎች ደግሞ የሥራ ዕድል እንዲሆኑ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 በሥራ ፈጣሪዎች ላይ የሚደርሰውን የባህል ተፅዕኖ በማንሳትም፣ አዳዲስ ፈጠራዎችን ለመሥራት ሲሞክሩ ከባህልና ከሃይማኖት ጋር በማገናኘት፣ የተለያዩ ስሞችን በመስጠትና እንደማይቻል አድርገው በማሳየት ለፈጠራ ሥራቸው እንቅፋት የሚሆኑ ብዙዎች ናቸው ብለዋል፡፡  

በዚህም ብዙ የፈጠራ ሥራ ያላቸው ወጣቶች ‹‹ሰው ምን ይለኛል›› በማለት ዕምቅ ዕውቀታቸውን ያላሳዩና ያላወጡ መኖራቸውንና የእነዚህን ወጣቶች ዕምቅ የፈጠራ ችሎታ በአደባባይ በማውጣት ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና አገራቸውን የሚጠቅም ሥራ እንዲያበረክቱ እያበረታቱ መሆኑን አክለዋል፡፡

አሁን ላይ ያሉ ወጣቶች ደፋር፣ ከቴክኖሎጂ ጋር ለመቀራረብ አዳዲስ ነገር ለመሞከር የሚታትሩ ናቸው፡፡ ዕድሉን ካገኙ ከመቀጠር ይልቅ የራስን ሥራ ፈጥሮ መሥራት የሚፈልጉ በመሆኑም የኢንተርፕርነርሽፕ ዋና ተግባሩም ለእነዚህ ወጣቶች ምቹ ሥነ ምኅዳርን መፍጠር ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም ‹‹አሁን ላይ አይቻልም›› የሚለው እንደ ቋሚ መልስ የተቀመጠበትን አዝጋሚ አሠራር በመቀየር በዘርፉ የሚሰማሩ ወጣቶችን በአጭር ጊዜ ውጤታማ ለማድረግ በቁርጠኝነት በመሥራት ላይ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡

አይቻልም የሚለውን ክፉ ሐሳብ በማስወገድ በዕውቀት ላይ የተገነባ ዓለም ውስጥ እየኖርን፣ ዕውቀት ያላቸውን ሰዎች ማበረታታት፣ አዳዲስ ሐሳብ ያላቸውን የፈጠራ ሥራቸውን ጥግ በማድረስ በማድረግ ለአገራቸው ትልቅ አቅምን እንዲፈጥሩ መሥራት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡

ለዚህ ሥራ መሳካት በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን በመፍታት፣  ብዙ ውጣ ውረድ የሚጠይቁ አሠራሮችን በማቃለል እንዲሁም የመሬትና ሌሎች ፈቃዶችን ለማግኘት የተጓተቱ አሠራሮችን በመቅረፍ ረገድ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ችግሮችን በአንክሮ ሊመለከት ይገባል ሲሉም ገልጸዋል፡፡  

አገሮች ካላቸው ምቹ የኢንተርፕርነርሽፕ ሥነ ምኅዳር ዝግጅት አኳያ በአፍሪካ ደረጃ የሚቀርብ መለኪያ አለ፡፡ በዚህ መለኪያ መሠረትም ኢትዮጵያ ወደ ኋላ ቀርታለች ብለዋል፡፡

እነዚህና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋቋመው የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ከተሠሩ ሥራዎች ይልቅ ዘንድሮ የተሠሩ ሥራዎች ውጤታማ ነበሩ ብለዋል፡፡

ውጤቱን ዘላቂ ለማድረግ በኢንተርፕርነርሽፕ፣ በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች ሥርዓተ ትምህርት በመዘርጋት ከሐሳብ እስከ ቢዝነስ ያለውን ጉዞ ምቹ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...