Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፕሪሚየር ሊጉ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚቋረጥ ተገለጸ

ፕሪሚየር ሊጉ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚቋረጥ ተገለጸ

ቀን:

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ከ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በኋላ እንደሚቋረጥ፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር አስታወቀ፡፡ ከጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ስድስተኛ ሳምንት ጀምሮ በድሬዳዋ ሲከናወን የቆየው መርሐ ግብሩ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚሰናዳው የአፍሪካ አገሮች ሻምፒዮና (ቻን) ምክንያት እንደሚቋረጥ ተገልጿል፡፡

የሊጉን ሁለተኛ ዙር ውድድር ከስድስተኛ እስከ አሥረኛ ሳምንት ድረስ ያሉትን መርሐ ግብሮች ለማከናወን ከባህር ዳር ተረክቦ ውድድሮችን ሲያከናውን የቆየው ድሬዳዋ ከተማ፣ እስከ 12ኛ ሳምንት ያሉትን ጨዋታዎች አስተናግዶ ታኅሣሥ 17 ቀን እንደሚያጠናቅቅ ታውቋል፡፡

በዚህም የሦስተኛ ዙር ጨዋታዎች ከ11ኛ ሳምንት ጀምሮ ማስተናገድ የነበረበት የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የነበረ ቢሆንም፣ ጨዋታዎቹ እንዳይቆራረጡ በሚል ሐሳብ በድሬዳዋ እንዲቀጥል መደረጉን የሊጉ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የሦስተኛውን ዙር የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን የሚያስተናግደው የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመጫወቻ ሜዳውና፣ ተያያዥ ነገሮች ላይ ዕድሳትና ማሻሻያ እንዲያደርግ በአክሲዮን ማኅበሩ መታዘዙ ይታወሳል፡፡ አክሲዮን ማኅበሩም ስታዲየሙ በሚፈለገው መጠን ማሻሻያና ዕድሳት ማድረጉን የአጣሪ ቡድኑ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ስታዲየሙም ውድድር ለማዘጋጀት የሚያስችለው ሁኔታ ላይ መድረሱን ማረጋገጡን አቶ ክፍሌ አሳስበዋል፡፡

እንደ ሥራ አስኪያጁ አስተያየት ከሆነ፣ ውድድሩን ለማስቀጠል ምቹ የሆነ የመጫወቻ ሜዳ ማግኘት ፈታኝ እንደሆነ ገልጸው፣ ሊጉን ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል፣ ውድድሩን የሚያዘጋጁ ከተሞች ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም ለማሰናዳት አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው ሥራ አስኪያጁ ይጠቁሟሉ፡፡

በሌላ በኩል የሊጉ ውድድሮች በዙር ሲከናወኑ፣ በተመልካች ዕጦት ሲመቱ መክረማቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይ ውድድሮቹ የሚከናወንባቸው ከተሞች ለተመልካች ቅርብ አለመሆናቸው ዋነኛ መንስዔ መሆኑ ተጠቅሶ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት አዲስ አበባ ለበርካታ ተመልካቾች አማካይ ከተማ በመሆኗ የተመልካች እጥረት ችግርን ሊቀርፍ ስለሚችል፣ የስታዲየሙ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ የሚጠናቀቅ ከሆነ አብዛኛውን የሊጉን ጨዋታ በአዲስ አበባ ለማድረግ ሐሳብ መኖሩን አክሲዮን ማኅበሩ ጠቁሞ ነበር፡፡

ከአዲስ አበባ ባሻገር የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ስታዲየም ሌላው ለተመልካች አማካይ የውድድር ቦታ በመሆኑ፣ የተወሰኑ ጨዋታዎች ላይ ሽግሽግ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሠረት 12ኛ ሳምንት ላይ ሊከናወኑ የነበሩ የቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ደርቢ ጨዋታ እንዲሁም የ11ኛ ሳምንት የወላይታ ድቻና ሲዳማ ቡና ጨዋታዎች ወደ አዳማ መዘዋወራቸውን አክሲዮን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

እንደ አቶ ክፍሌ አስተያየት ከሆነ፣ በመጠኑም ቢሆን በተመልካች ዕጦት ሲቸገር የነበረው የሊጉ ውድድር እየተሻሻለ መምጣቱን የገለጹ ሲሆን፣ የሊጉ ውድድሮች በአዳማና አዲስ አበባ ሲቀጥሉ የተመልካቾች ቁጥር እንደሚጨምር እምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

ከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ፣ አልጄሪያ ለምታዘጋጀው የአፍሪካ አገሮች ሻምፒዮና (ቻን) ለመሳተፍ ቅድመ ዝግጅት ለ42 ተጫዋቾች ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከታኅሣሥ 18 ጀምሮ መደበኛ ዝግጅታቸውን እንደሚጀመሩ ገልጸዋል፡፡

በአገር ውስጥ ሊግ ላይ የሚሳተፉ ተጫዋቾችን ብቻ በሚያሳትፈው ውድድር፣ ከጥር 5 እስከ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በአልጄሪያ የሚከናወን ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአስተናጋጇ አልጄሪያ፣ ሞዛምቢክና ሊቢያ ጋር ተደልድላለች፡፡

በዚህም መሠረት ዋሊያዎቹ በሻምፒዮናው ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ በተመለሱ ከአምስት ቀናት በኋላ የቤትኪንግ መርሐ ግብር እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ሊጉ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብሩን ሰኞ ታኅሣሥ 17 ቀን በድሬዳዋ ካጠናቀቀ በኋላ፣ ብሔራዊ ቡድኑ ከቻን ውድድር ከተመለሰ በኋላ በአዳማ ሳይንስና ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 13ኛ ሳምንት መርሐ ግብርን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...