Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበትምህርት ቤቶች ክበባት ቦታ ያልተሰጠው ሰብዓዊ መብት

በትምህርት ቤቶች ክበባት ቦታ ያልተሰጠው ሰብዓዊ መብት

ቀን:

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና እየሰፋ መጥቷል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም ስለመግባታቸው ምንም ዓይነት ዋስትና እንደሌላቸው የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡

በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሠለጠኑ አገሮች ከደረሱበት ደረጃ መድረስ ቀርቶ፣ አሁን ላይ ለሰው ልጅ ቀዳሚውና መሠረታዊ የሆነውን በሕይወት የመኖር ዋስትናና አካላዊ ደኅንነት ማስጠበቅ ላይ ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ መግባቷ ይታወቃል፡፡ በዚህም ምክንያት ከተፈጥሯዊ የሰው ልጅ ነፃነትና ክብር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የመብቶችና ዴሞክራሲዊ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በግልና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 370 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ለስድስት ወራት አሠልጥኖ ታኅሣሥ 1 ቀን 2015 ዓ.ም.  አስመርቋል፡፡

የካርድ ዋና ዳይሬክተር አቶ በፈቃዱ ኃይሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታሰበውን የሰብዓዊ መብቶች ቀንና የተማሪዎች ምረቃ አስመልክተው እንደገለጹት፣ በረዥም ዓመታት የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሰብዓዊ መብቶችን የሚያከብር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማኅበር የመገንባቱ ሒደት እስካሁን አልተሳካም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በየጊዜው የሚከሰቱ የፖለቲካ ለውጦች ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ያላቸው ቁርጠኝነት እምብዛም አይደለም የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በዚህም የተነሳ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ለሰብዓዊ መብቶች የሚታገሉ ተቋማትና ግለሰቦች ቁጥር ዝቅተኛ እንደሆነ፣ ይህም ከተፈጥሯዊ የሰው ልጅ ነፃነትና ክብር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን መንግሥት እንዲመልስና እንዲያከብር እንዲሁም ደግሞ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ሁኔታዎችን እንዲያሟላ የሚያደርግ ትውልዳዊ መሠረት አልተጣለም ማለት ይቻላል ሲሉ አክለዋል፡፡

ዜጎች አቅማቸው አድጎና መብቶቻቸውን በቅጡ ተረድተው እንዲሟገቱ እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓተ ማኅበር እንዲገነቡ ለማድረግ ተቋሙ አምስት ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አቶ ፈቃዱ ተናግረዋል፡፡

የፕሮጀክቶቹም ዓላማ ወጣቶች መብቶቻቸውን እንዲያውቁና እንዲጠይቁ ማድረግ መሆኑን፣ ባለፉት ዓመታትም በነበረው ጦርነት ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲከሰቱ መንግሥት ትክክለኛ አሠራርን እንዲከተል መወትወታቸውን አብራርተዋል፡፡

የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከልና ያሉትን ችግሮች ለማኅበረሰቡ ለማሳወቅ በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በደብረ ብርሃን፣ በሐዋሳ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋና በቢሾፍቱ የሚገኙ የግልና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ላይ የሚማሩ 370 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ሥልጠና ሰጥቶ ማስመረቁን ተናግረዋል፡፡

‹‹የአዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ›› ተከታታይ ሥልጠና ላይ የታደሙ ተማሪዎች በየትምህርት ቤቶቻቸው የሰብዓዊ መብቶች ክበቦች እንዲያቋቁሙ ለማድረግ ተቋሙ ጥረት እያደረገ ቢሆንም፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ መበቶች ክበቦች እንዲቋቋሙ መንግሥት ፈቃደኛ አለመሆኑን አቶ ፈቃዱ አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን በየትምህርት ቤቱ ክበቦች እንዲቋቋም የፈቀደው አሥራ አንድ ዓይነት ክበቦችን ብቻ መሆኑን፣ ከእነዚህም ክበቦች ላይ የሰብዓዊ መብቶች ክበብ አለመካተቱ ትልቅ ችግር እንደሆነባቸው አብራርተዋል፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ክበብ በየትምህርት ቤቱ ባለመቋቋሙ የተነሳ በተቋሙ በኩል ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች ትምህርት ቤቶቻቸው ላይ ሊሠሩ ቢፈልጉም ሳይሳካላቸው መቅረቱንና ከባድ ችግር ውስጥ መሆናቸውን አቶ ፈቃዱ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡  

ትምህርት ሚኒስቴርም ይህንን ታሳቢ በማድረግ እንደ አዲስ ፖሊሲዎችን በመከለስ የሰብዓዊ መብቶች ክበብ እንዲቋቋም መፍቀድ ይኖርበታል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ‹‹የሰብዓዊ መብቶች ባህል ማለት አንድም ባለመብቱ ያለ ሥጋትና ፍርኃት መብቱን መጠየቅና የሚጠይቀውን መብትና ግዴታ ፈጻሚ አካላት የሚያውቅበት ሁኔታ መፍጠርን ያካተተ ነው፡፡

በሌላ በኩል ሰብዓዊ መብቶችን የመጠበቅ፣ የማክበር፣ የማስበርና የማሟላት ግዴታ ያለባቸው አስፈጻሚ አካላት የሁሉንም ሰዎች መብት አውቀው፣ ተረድተውና አምነውበት የሚተገብሩበት ብቻ ሳይሆን፣ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ሳይተገብሩ ቢቀሩ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አምነው መሥራት ይኖባቸዋል ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

የዚህ ዓይነት ባህል ሲሰፍን የሰብዓዊ መብቶች መጠበቅ፣ መከበርና መሟላት እንደ መደበኛ ሁኔታ የሰብዓዊ መብቶች መጣስ ደግሞ እንደ ልዩ ሁኔታ የሚታይበት መንገድ ይፈጠራል ብለዋል፡፡

‹‹የአዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ›› ተከታታይ ሥልጠና በ2013 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን በመጀመርያው ዙር ተከታታይ ሥልጠና 364 በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሥልጠናውን እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ከመጀመርያው ዙር ሠልጣኞች መካከል በየትምህርት ቤቶቻቸው የሰብዓዊ መብቶች ግንዛቤ ማሳደጊያ ንቅናቄዎችን የጀመሩ እንዳሉም በወቅቱ ተገልጿል፡፡

ሥልጠናውን በ2015 ዓ.ም. በመቀጠልን ተደራሽነትን በማስፋት እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...