ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር በአሜሪካ ተቋማት “የአፍሪካ የላቀ አመራር” ሲሸለሙ የተናገሩት፡፡ ‹‹አፍሪካ፡ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት›› በሚል መሪ ቃል አሜሪካን አካዳሚ ኦቭ አቺቭመንት እና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙት ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም. በጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ በአራት ዓመታት ውስጥ 25 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የአራት ዓመት ዕቅዷን አሳክታለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ማሳረጊያም፣ ዘመናዊ ሥልጣኔን ከምድሪቱ ሥርዓተ ምህዳር ጋር ለማስማማት ለሚኖረው ዓለም አቀፋዊ ንቅናቄ የአረንጓዴው አሻራ መርሐ ግብር እንደሚያተጋ አንዳች ጥርጣሬ እንደማይኖራቸውም አስምረውበታል።