Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የተወሰኑ የባልደራስ ፓርቲ አባላትን ማሰሩን...

ከአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የተወሰኑ የባልደራስ ፓርቲ አባላትን ማሰሩን ፖሊስ አስታወቀ

ቀን:

በአዲስ አበባ በሚገኙ የተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ከሰሞኑ ተቀስቅሶ ከነበረው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት ያላቸውን የባልደራስ ፓርቲ አባላት በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የከተማዋ ፖሊስ ማከሰኞ ዕለት አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተቀሰቀሰውና ላለፉት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ተቃውሞና ረብሻ መረጋጋቱን የገለጸ ሲሆን፣ ከታኅሳስ 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማሩ ተግባር በሰላም ሲካሄድ መዋሉን አስታውቋል።

ከሰሞኑ የነበረው ተቃውሞ የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶችን ‹‹የረብሻና የጥፋት ብሎም የውድመት መድረክ ለማድረግ›› የታቀደ ነበር የሚለው መግለጫው፣ በታቀደው በዚህ ሕገወጥ ተግባር ላይ ቀጥታኛ ተሳትፎ ማድረጋቸው በማስረጃ የተረጋገጠባቸው፣ አንዳንድ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አባላት›› እጅ ከፍንጅ ተይዘው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን አስታውቋል። ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ስላዋላቸው የባልደራስ ፓርቲ አባላት ማንነትና ብዛት አልገለጸም።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከባልደራስ ፓርቲ አባላት በተጨማሪም፣ በድርጊቱ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበራቸው የተባሉ አንዳንድ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ከትምህርት ቤት ውጭ ሆነው ችግሩን በማቀጣጠልና ወደ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ሰብረው በመግባት በትምህርት ቤቶቹ ሀብት ላይ ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ አድርገዋል የተባሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ተጨማሪ ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የጀመረውን ዕርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀው ፖሊስ፣ የተማሪ ቤተሰቦችና ኅብረተሰቡ እውነታውን በመረዳት ልጆቹን በመምከር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስቧል።

በማከልም፣ ‹‹በሕጋዊ ሽፋን የኅብረተሰቡን ሰላምና ደኅንንት በሚያውኩ ልዩ ልዩ ሕገወጥ ተግባር ላይ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድኖችና ግለሰቦች ከአጥፊ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል፤›› ሲል አሳስቧል፡፡ 

ፖሊስ ይህን ይበል እንጂ፣ በፌዴራሉ መንግሥት የተቋቋመውና በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነው የኢትዮጵያ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ጨምሮ፣ በአገሪቱ ሕግ መሠረት ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባወጧቸው መግለጫዎች፣ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ለተቀሰቀሰው ተቃውሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ተጠያቂ አድርገዋል።

ከሰሞኑ ለነበረው ተቃውሞ መነሻ ምክንያቱ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል መዝሙር በአስገዳጅ ሁኔታ እንዲዘመርና የክልሉ ሰንደቅ ዓላማ እንዲውለበለብ ተደርጎል የሚል አቤቱታ ሲቀርብ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ በተከማዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ የፖለቲካ ግብ የያዙ ኃይሎች የፈጠሩት እንደሆነ ይገልጻል።

ሕዝብ በእጅጉ የተማረረበትን ሌብነት እና ሙስናን ለመዋጋት መንግስት የጀመረው ዕርምጃ ያስደነገጣቸውና መንግሥት የአገራችንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችለው የሰላም ስምምነት ያልተዋጠላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች አሉታዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

የከተማችን ብሎም የአገራችን ሰላም መሆን እንቅልፍ የሚነሳቸው እነዚህ ፀረ ሰላም ኃይሎች ማንነት ላይ ያተኮረ እኩይ አጀንዳ ቀይሰው ትምህርት ቤቶችን የሁከትና የብጥብጥ መድረክ ለማድረግ ላይ ታች ሲሉ ቆይተዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...