Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሲቪል ማኅበራት ራሳቸው የሚፈጥሩትን የጥቅም ግጭት የሚፈታ ሥርዓት እንዲያበጁ የሚያስገድድ በመመርያ ወጣ

የሲቪል ማኅበራት ራሳቸው የሚፈጥሩትን የጥቅም ግጭት የሚፈታ ሥርዓት እንዲያበጁ የሚያስገድድ በመመርያ ወጣ

ቀን:

ሁሉም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የጥቅም ግጭቶች ሲፈጠሩ፣ የሚፈቱበትና አስተዳደራዊ ዕርምጃዎችን የሚወስዱበት ሥርዓት በራሳቸው እንዲፈጥሩ የሚያስገድድ መመርያ ወጣ፡፡ ከዚህ በፊት ሕግ ስላልወጣና የማይገደዱ ቢሆንም፣ በዚህ መመርያ ግን ሁሉም ማኅበራት ወጥ በሆነ መንገድ ሥርዓት እንዲዘረጉ ይገደዳሉ፡፡

በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ፀድቆ የወጣው መመርያ፣ በድርጅቶቹ ውስጥ ከጥቅም ግጭት ጋር በተያያዘ፣ የድርጅቱ አባላት የሆኑ የሥራ መሪዎች፣ ሠራተኞች፣ ሌሎች አካላት አቤቱታ ሲያቀርቡ፣ የሚያጣራ ውሳኔ ሰጪ አካል እንዲያቋቁሙ ያዛል፡፡ የውሳኔ ሰጪ አካሉም ሥራ አስኪያጅን፣ ሥራ አስፈጻሚን፣ ቦርድን ወይም ጠቅላላ ጉባዔን ያካትታል፡፡

እንደ ባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ገለጸ፣ ባለሥልጣኑ ከዚህ በኋላ እንደ ግዴታ አሠራር የሚያየው አንደኛው የጥቅም ግጭት የሚቀረፍበትን ሥርዓት ነው፡፡ ማኅበራት ይህን ካላደረጉም እንደ ጥፋት ተቆጥሮ አስተዳደራዊ ዕርምጃ የሚያስወስድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹የተወሰኑ የሲቪል ማኅበራት ሥርዓት ዘርግተውና ፖሊሲ አውጥተው ይህን ሲተገብሩ ነበር፡፡ አብዛኛው ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ የዳበረ ሥርዓት አልነበራቸውም፤›› ብለዋል፡፡

የሲቪል ማኅበራቱ በውስጥ አሠራራቸው ዕርምጃ የሚወስዱበትን አግባብና አጠቃላይ የተወሰደውን ዕርምጃ ለባለሥልጣኑ በዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲያሳውቁ መመርያው ያዛል፡፡ ከዚህ በፊት ግን ይህ በግዴታ እንዳልነበረ አቶ ፋሲካው ገልጸዋል፡፡ ‹‹እነሱ በራሳቸው ኮሚቴም ሆነ ሌላ አደረጃጀት አዋቅረው ጥቆማዎችን ተቀብለውና አጣርተው የወሰዱትን ዕርምጃ፣ ለእኛ እንደ ተቋም በዓመት ሪፖርት ማሳወቅ ነው ያለባቸው፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

በተቋማቸው ሁሉንም ነገር ተቆጣጥሮና አጣርቶ መሄድ የማይታሰብ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ፋሲካው፣ የሲቪል ማኅበራት ሠራተኞች ከራሳቸው የግል ጥቅም ይልቅ የድርጅቶችን ተቋማዊ ጥቅም አስቀድመው መሥራት እንዳለባቸው ኃላፊነት የሚጥል መመርያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ መንግሥትም በጊዜ ሒደት በማኅበራት ላይ የሚያደርገው ቁጥጥር እየቀነሰ፣ ድርጅቶች ራሳቸውን የሚያስተዳድሩና በታማኝነት የሕዝብ ተቀባይነት እንዲያገኙ እንደሚፈለግ አክለዋል፡፡ ‹‹በራሱ መንገድ ተገዥ የሆነ የሲቪል ማኅበር ድርጅት መፍጠር ነው የባለሥልጣኑ ዋነኛ ፍላጎት፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሆኖም በመመርያው ላይ እንዳሠፈረው ባለሥልጣኑ ከጥቅም ግጭት ጋር በተያያዘ የቀረበለት ጥቆማ ካለ ለድርጅቶቹ መርምረው ውሳኔ እንዲያሳልፉ የሚነግራቸው ሲሆን፣ ድርጅቶቹም የተሰጠውን ውሳኔ ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ አለባቸው፡፡ ድርጅቶቹም ተገቢ ምርመራ ካላካሄዱና ውሳኔ ካልሰጡ፣ ባለሥልጣኑ በራሱ መርምሮ ውሳኔ ሊሰጥ እንደሚችል መመርያው ላይ ተመልክቷል፡፡

መመርያው የጥቅም ግጭት መከሰትን ሲያስረዳ፣ አንድ የድርጅት አባል የድርጅቱን ተልዕኮ በሚያስፈጽም ጊዜ የግሉ የፋይናንስ ወይም ሌላ ዓይነት ጥቅም የሚኖረው ከሆነ፣ እንዲሁም የአባሉ ቤተሰብ አባል በንግድ ወይም ሌላ ግንኙነት መንገድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሲገናኝ ነው፡፡ የቤተሰብ አባል በማለት የተካተቱት የአባሉ የትዳር ጓደኛ፣ እናት፣ አባት፣ እህት፣ አክስት፣ አጎት፣ ልጅና ሌሎች በሥጋ ወይም በቅርበት የሚገናኙ የቤተሰብ አባላት ናቸው፡፡

የጥቅም ግጭት መንስዔዎች ተብለው ከተዘረዘሩት ተግባራት ውስጥም፣ ከድርጅቱ ጋር የሥራ ግንኙነት ካላቸው ሦስተኛ ወገኖች የግል ስጦታዎችን መቀበል ወይም መበደር፣ እንዲሁም ከእነዚህ ሦስተኛ ወገኖች ውስጥ አክሲዮንና የንብረት ጥቅም መያዝ ወይም ዕዳ መኖር አለበት፡፡

ውሳኔ ሰጪ አካሉ የጥቅም ግጭት መኖር አለመኖሩን ለመወሰን አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው፣ ጉዳዩን መርምሮ የተለያዩ አማራጮችን ያካተተ የውሳኔ ሐሳብ የሚያቀርብ ገለልተኛ ሰው ወይም ኮሚቴ እንዲሰይም በመመርያው ተመልክቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...