ፌደራላዊው ሕገመንግሥት የፀደቀበት ኅዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም. መሠረቱ ያደረገውና እስከ 1988 ዓ.ም. ድረስ ‹‹የሕገ መንግሥት ቀን›› ይባል የነበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሐዋሳ ከተማ በሚገኘው ስታዲየም ተከብሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድና የክልል መሪዎች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በዓል ላይ ልዩ ልዩ ትርዒቶች ቀርበዋል፡፡ ፎቶዎቹ የቀኑን ገጽታ በከፊል ያስቀኛሉ፡፡