Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየብልፅግና ተወካይ በወቅታ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስብሰባ...

የብልፅግና ተወካይ በወቅታ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስብሰባ ጠራ

ቀን:

በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ተጠናክሮ በቀጠለው የንፁኃን ዜጎች ጭፍጨፋ፣ እንዲሁም በአገሪቱ በነገሠው የሰላም ዕጦትና አለመረጋጋት ላይ የጋራ አቋም ለመያዝና የብልፅግና ፓርቲ ተወካይ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ለሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ መጥራቱን፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

በምክር ቤቱ መንግሥት የመሠረተው የብልፅግና ፓርቲ ተወካይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ለመጠየቅ፣ አገሪቱን በገጠሟት ችግሮች ላይ ተነጋግሮ የጋራ አቋም ለመያዝና መፍትሔ ለማፈላለግ እንዲቻል ስብሰባው መጠራቱ ታውቋል፡፡

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ተወካይና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ መብራቱ ዓለሙ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ለብሔር ብሔረሰቦች በዓል የሥራ አስፈጻሚ አባላቱ እንደሚገኙ ተስፋ በማድረግ፣ በሐዋሳ ከተማ አስቸኳይ የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ቢጠራም፣ ሁሉም ሊገኙ ባለመቻላቸው ለሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ስብሰባውን ለማዛወር ተገደዋል፡፡

‹‹በተለይ የብልፅግና ፓርቲ ተወካይ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በሥራ መደራረብ ሊገኙ ባለመቻላቸው፣ አገር እየመራ ያለውን ፓርቲ ስለአገራዊ ችግሮች የሚሰጠውን ማብራሪያ ለማድመጥ ሲባል ስብሰባውን አዛውረናል፤›› ብለዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተጠናክሮ የቀጠለውን የንፁኃን ዜጎች ግድያ እንደሚያወግዝ፣ የተለያዩ ፓርቲዎችም በተናጠል ድርጊቱን እያወገዙት መሆናቸውን የተናገሩት ሰብሳቢው፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ፓርቲዎች ተሰብስበው መምከርና የጋራ አቋም መያዝ እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡

‹‹በሥራ አስፈጻሚ ስብሰባችን በወለጋና በአሳሳቢ አገራዊ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን፡፡ መንግሥት የመሠረተው ብልፅግና ፓርቲ የሚሰጠውን ማብራሪያ እናደምጣለን፡፡ ከተስማማን ተስማማን፣ ካልተስማማን ደግሞ ሁሉንም (53) የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ፓርቲዎችን ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት በጉዳዩ ላይ እንዲመከርበት እናደርጋለን፤›› ሲሉ ነው መብራቱ (ዶ/ር) የተናገሩት፡፡

በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን ባለፈው ሳምንት በኦነግ ሸኔ በተፈጸመ ጥቃት ከ200 በላይ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፋቸው መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፣ ባለፉት አራት ዓመታት ወለጋን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተመሳሳይ አሰቃቂ ጥቃቶች መድረሳቸው ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...