Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበኮስሞ ትሬዲንግ ድርጅት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በተባሉ ግለሰቦችና ተቋም ላይ የ79.7 ሚሊዮን...

በኮስሞ ትሬዲንግ ድርጅት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በተባሉ ግለሰቦችና ተቋም ላይ የ79.7 ሚሊዮን ብር ክስ ተመሠረተ

ቀን:

ያልተገባ ጥቅምና ብልፅግና ለማግኘትና ለሌሎችም ለማግኘት በማሰብ፣ የኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ላይ ከ79.7 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦችና ድርጅት ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

ክሱ የተመሠረተው ጄጄ ፕሮፐርቲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ወ/ሮ አዜብ ምሕረተአብና አቶ ተመስገን ይልማ በሚባሉ ድርጅትና ግለሰቦች ላይ ሲሆን፣ ኮስሞ ትሬዲንግ ድርጅት ላይ ሊተካ የማይችል ከፍተኛ ኪሣራና አደጋ እንዳደረሱበት፣ የተከሳሽ ከሳሾች አቶ ኃይለየሱስ መንግሥቱ፣ ኖኤል ኃይለየሱስና አቤል ኃይለየሱስ የተባሉ ግለሰቦች ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አምስተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት አሻሽለው የመሠረቱት ክስ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ ከዓመታት በፊት ባላቸው ደኅንነትና ፖሊስ አስገድደው አቶ ኃይለየሱስን በማስፈረምና ሥልጣናቸውን በመጠቀም 500 ሚሊዮን ብር ግምት ያለውን ባለ ዘጠኝ ወለልና ባለአራት ኮከብ ዋን ሃው ሆቴልና ቢሮ ዋስትና በማስያዝ 61 ሚሊዮን ብር ተበድረው 32,500,000 ብር መውሰዳቸውንና ክስ ተመሥርቶባቸው በቀጠሮ ላይ መሆኑም በክሱ ተብራርቷል፡፡

በንብረታቸው ላይ የተጣለው ዕግድ ሊነሳ ባለመቻሉ 32,500,000 የባንክ ዕዳ እንዳለባቸውና አቶ ኃይለየሱስም አከራይተውት የነበረውን ዋን ሃው ባለ አራት ኮከብ ሆቴል፣ ተከሳሾች አከራይተው 17,880,000 ብር ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ክስ ተመሥርቶባቸው በምርመራ ላይ መሆኑንም ከሳሾች አብራርተዋል፡፡

የኮስሞ ትሬዲንግ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ተመሥገን ይልማና ወ/ሪት አዜብ ምሕረተአብ ከውል ውጪ በዋን ሃው ሆቴል በኪራይ ለቆዩበት እስከ መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በድምሩ 29,000,000 ብር እንዲከፈላቸው ክስ መሥርተው እየተመረመረ መሆኑን ጠቁመው፣ ድርጅቱ ለሦስት ዓመታት ንግድ ፈቃዱ ባለመታደሱ የቅጣትና ማደሻ፣ እንዲሁም አቶ ኃይለየሱስም ለ48 ወራት ያልተከፈላቸውን 960,000 ብር ደመወዝን ጨምሮ ከላይ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ክሱን ተቀብሎ በቀረበው የክስ አቤቱታ ላይ ለማከራከር ለታኅሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...