Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየፔሌ ምኞትና የብራዚል የኳታር ዓለም ዋንጫ ጉዞ

የፔሌ ምኞትና የብራዚል የኳታር ዓለም ዋንጫ ጉዞ

ቀን:

የ20ኛው ክፍለ ዘመን ድንቅ ተጫዋችና የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ዓርማ ነው፡፡ የክፍለ ዘመኑ ምርጥ አትሌት የሚል ስያሜንም አግኝቷል፡፡

በ1999 በተመሳሳይ ዓመት ታዋቂው ‹‹ታይሞ›› ጋዜጣ የክፍለ ዘመኑ መቶ ምርጥ ሰዎች ውስጥ የፔሌን ስም አካቷል፡፡

ፔሌ የብራዚልን መለያ ለብሶ በስዊድን የዓለም ዋንጫ (1958)፣ በቺሌ ዓለም ዋንጫ (1962) እንዲሁም በ1970 ሜክሲኮ ዓለም ዋንጫ ማሳካት የቻለ የክፍለ ዘመኑ ድንቅ ተጫዋች በመሆኑ ታሪክ ሲዘከር ይኖራል፡፡ ፔሌ 1,363 ጨዋታዎችን ተጫውቶ 1,279 ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ በዓለም የጊነስ ክብረ ወሰን መዝገብ ላይ ስሙ መቀመጥ ችሏል፡፡

ዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር ስሙ የሚነሳው ፔሌ 82 ዕድሜው ላይ ሲገኝ፣ ከቀናት በፊት በፅኑ ታሞ ሆስፒታል ገብቷል፡፡

ብራዚል በኳታር ዓለም ዋንጫ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ከመጫወቷ አስቀድሞ ፔሌ በማኅበራዊ ሚዲያው አንድ መልዕክት አስቀምጦ ነበር፡፡

‹‹በ1958 በስዊድን ጎዳናዎች ስንሸራሸር ለአባቴ የገባሁትን ቃል ለማሟላት እያሰላሰልኩ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ብሔራዊ ቡድኖች ተመሳሳይ ቃል እንደሚገቡና የዓለም ዋንጫውን ለማሳካት እንደሚፈልጉ አውቃለሁ፡፡ እኔም ጓደኞቼን እናንተን ማነሳሳት እፈልጋለሁ፤›› ሲል ነበር ለብሔራዊ ቡድኑ የገለጸው፡፡

የጥሎ ማለፉን ጨዋታ ከሆስፒታል ሆኖ እንደሚመለከት ያሠፈረው ፔሌ፣ ‹‹በዚህ ጉዞ ላይ አብረን ነን፡፡ መልካም ዕድል ለብራዚል፤›› ሲል ለአገሩ ብሔራዊ ቡድን ምኞቱን ገልጿል፡፡

ሁሌም ለብሔራዊ ቡድኑ መልካም ምኞቱን ከመግለጽ የማይቆጠበው ፔሌ፣ በአንድ ወቅት የአሁኑ የብራዚል የክንፍ አጥቂ ቪንሺየስ ጁኒየር የዘረኝነት ስድብ ባደረሱበት ወቅት ከዓላማው ፈቀቅ እንዳይል ሲያበረታታው ነበር፡፡

‹‹እግር ኳስ ደስታ ነው፣ ዳንስ ነው፣ እውነተኛ ድግስ ነው፣ ተጫዋች ግብ ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን በዳንስ መግለጽ ከፈለገ ሊከበርለት ይገባል፤›› በማለት ለተጫዋቾች ዘብ የቆመበት ጊዜ ይታወሳል፡፡

‹‹ዘረኝነት ፈገግታችንን ሊቀማን አይገባም፡፡ ደስታችንን በፈለግነው መንገድ መግለጽ እንችላለን፤›› በማለት በተጫዋቾች ላይ የሚደርሰውን ስድብ ሲከላከል ቆይቷል፡፡

ፔሌ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ የለጠፈው መልዕክት የተመለከቱት የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾ ደቡብ ኮሪያን 4 ለ 1 ከረቱ በኋላ የፔሌን ምሥል አንግበው ያላቸው ክብር ገልጸውለታል፡፡

በካንሰር ሕመም እየተሰቃየ የሚገኘው ፔሌ፣ በሳኦ ፖሎ ሆስፒታል ሕክምናው እየተከታተለ የሚገኝ ቢሆንም በፅኑ መታመሙ ግን ተገልጿል፡፡

በዚህም ምክንያት የብራዚሉ ምክትል አሠልጣኝ ፔሌ ከሕመሙ እንዲያገግም ተጫዋቾች ፀሎት እንዲያደርጉለት ጥሪ አቅርቦላቸዋል፡፡

የአምስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለዕድሏ ብራዚል እ.ኤ.አ. 1958፣ 1962፣ 1970፣1994 እና 2002 የዓለም ዋንጫውን ማንሳት ችላለች፡፡

በ2014 ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ 7 ለ1 ሸንፈት የደረሰባት ብራዚል፣ በ2018 የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ዋንጫውን እንደምታነሳ ግምት ብታገኝ ከምድቧ ማለፍ ተስኗት ወደ አገሯ ተመልሳለች፡፡ 

በዘንድሮ የኳታር ዓለም ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድን ወደ ሩብ ፍፃሜ ከገቡ ቡድኖች መካከል አንደኛው ሆኗል፡፡ በድንቅ ብቃትና ልምድ ባላቸው ተጫዎቾች የተሞላው የብራዚል ብሔራዊ ቡድን የኳታርን ዓለም ዋንጫ እንደሚያነሳ ቅድሚያ ግምት የተሰጠው ቡድን ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...