Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢዜማ በምሥራቅ ወለጋ ዞን የንፁኃን ጭፍጨፋ አሳስቦኛል አለ

ኢዜማ በምሥራቅ ወለጋ ዞን የንፁኃን ጭፍጨፋ አሳስቦኛል አለ

ቀን:

  • በግጭት ቀጣና ውስጥ ያሉ ዜጎች ራሳቸውን ከጥቃት ለመጠበቅ መታጠቅ አለባቸው ብሏል

በአበበ ፍቅር

በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን እንደገና ተጠናክሮ የቀጠለው የንፁኃን ዜጎች ጭፍጨፋ እንዳሳሰበው፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አስታወቀ

ኢዜማ ይህንን ያለው ሰሞኑን በምሥራቅ ወለጋ ባሉ ዞኖችና ወረዳዎች የደረሰውን የንፁኃን ዜጎች ጭፍጨፋ በማስመልከት፣ ማክሰኞ ኅዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

የዜጎችን ከቀያቸው መፈናቀልና የጅምላ ግድያ አስመልክቶ በተለያዩ ጊዜያት የመፍትሔ ሐሳብ ሲያቀርብ እንደነበር ያስታወሰው ፓርቲው፣ አሁንም የዜጎችን ደኅንነት ማስከበር ያልተቻለው፣ ሽብርተኞችን የሚደግፉ አካላት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በመሰግሰጋቸው ነው ብሏል፡፡

አሁን በርካታ ዜጎች በኦነግ ሸኔ ታግተው እንደሚገኙ ያስታወቀው ኢዜማ፣ አሸባሪው ቡድን በየጊዜው በሚያደርገው እኩይና አፍራሽ እንቅስቃሴዎች ዜጎች፣ በአገራቸው ላይ ተስፋ በመቁረጥ ወደ ለየለት ብጥብጥ እንዲገቡ፣ በተለያዩ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ እየተደገ የሚተገበር ነው ሲል ኢዜማ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

‹‹ይህንን ከፋፋይ የሆነ ተግባር እንደ መጨረሻ አማራጭ ወስደው በሰፊው እየተገበሩት እንደሆነ ቅንጣት አንጠራጠርም፤›› ብሏል፡፡ በንፁኃን ላይ የሚደርስን ግፍ ያስቆማል ተብሎ የሚታሰብ የፀጥታ ኃይል፣ ከግፈኞች ጎን በመቆም ንፁኃንን የማፈናቀልና ግድያዎችን መከላከል አለመቻል እንደ አገር አስፈሪ ተግባር ነው ሲሉ የኢዜማ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ተናግረዋል፡፡

ከፕሪቶሪያው ስምምነት ማግሥት በወለጋ በኩል በእጅጉ የተስፋፋው የዜጎች ሞትና መፈናቀል፣ አገሪቱ በዘላቂነት ወደ ሰላም እንዳትመለስ ታስቦ እየተሠራበት ነው ሲሉ አክለው ተናግረዋል፡፡ በግጭቱም ዜጎች መንግሥት የለም የሚል አንድምታ እንዲይዙና በብሔራቸው ብቻ እንዲያስቡ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡

የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት በዋናነት የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ቢሆንም፣ በተጨባጭ እየታየ ያለው እንቅስቃሴ አናሳ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

በተለያዩ ቦታዎች በዜጎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም መንግሥት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለዜጎች በሚገባቸው መንገድ ማስረዳት ይኖርበታል ብለዋል፡፡ አገረ መንግሥቱን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ለማስቆምና የዜጎችን ጭፍጨፋ ለማስቀረት፣ ሁሉም ዜጋ በአንድነት ሊታገል ይገባል ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ‹‹እነዚህ አፍራሽ ኃይሎች እንደ አገር አጥብቀው የያዙንን የሞራል መሠረቶች በማናጋት አገርን ለመበታተን እየሠሩ ነው፤›› ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የመንግሥት ኃይል ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ፈጥኖ መድረስ ካልቻለ፣ ዜጎች ራሳቸውን ሊከላከሉ የሚችሉበትን ሁኔታ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ማመቻቸት አለበት ሲሉ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...