ድቁስቁስ ያሉት አሮጊት ሁለት ሰዓት ሙሉ አውቶቡስ ሲጠብቁ ቆይተው በመጨረሻ ተጋፍተው መሳፈር ቻሉ፡፡ ከዚያም ግንባራቸው ላይ ችፍ ያለውን ላብ እየጠረጉ፣ ‹‹ተመስገን ፈጣሪ፣ ክብር ምሥጋና ይድረስህ አምላኬ!›› አሉ፡፡
የአውቶቡሱ ሾፌር፣ ‹‹እማማ እንደዚያ ማለት የለብዎትም፡፡ ክብር ምሥጋና ለጓድ ስታሊን ይድረሰው! ማለት ነው ያለብዎት›› አላቸው፡፡
‹‹ይቅርታ፣ ጓድ›› አሉ ሴትየዋን፣ ‹‹እኔ ኋላቀር አሮጊት ነኝ፡፡ ከእንግዲህ የነገርከኝን እፈጽማለሁ፡፡›› ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሴትየዋ ‹‹ይቅርታ ጓድ፣ እንደምታየኝ ደደብ አሮጊት ነኝ፡፡ አያድርገውና ስታሊን ቢሞት ምንድነው ማለት ያለብኝ?›› ሲሉ ጠየቁ፡፡
‹‹ያኔ ተመስገን ፈጣሪ ማለት ይችላሉ፣ እማማ፡፡››
- አረፈ አይኔ ሐጐስ ‹‹ፖለቲከኞች እፈሩ››