- በአንድ ወቅት በአንድ መንደር የሚኖሩ ሰዎች ዝናብ በመጥፋቱ ምክንያት ፀሎት ሊያደርጉ ወሰኑ፡፡ ፀሎቱ በሚያደርጉበት ቀን ሁሉም የመንደሩ ሰዎች ተሰባሰቡ፣ አንድ ትንሽ ልጅ ብቻ ዣንጥላ ይዞ ተገኘ፡፡ ይህ እምነት ይባላል፡፡
- ሕፃን ልጅህን ወደላይ እየወረወርህ ስታጫውታት በደስታ ትፍነከነካለች እንጂ አታለቅስም፡፡ ምክንያቱም መልሰህ እንደምትቀልባት ታውቃለችና!! ይህም እርግጠኝነት ይባላል፡፡
- በእያንዳንዱ ምሽት ወደ አልጋችን ስንሄድ በነገው ማለዳ በሕይወት እንደምንቆይ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባይኖረንም አላርም (የማንቂያ ደወል) ሞልተን እንተኛለን!! ይህም ተስፋ ይባላል፡፡
- ወደፊት ምን እንደምንሆን (እንደሚሆን) እውቀት ሳይኖረን ታላላቅ እቅዶችን እንነድፋለን!!! ይህ ደሞ በራስ መተማማን ይባላል፡፡
- ዓለም ላይ የሚወርደውን መከራና ስቃይ እናያለን፤ ይሁን እንጂ አሁንም እንጋባለን፡፡ ይህም ፍቅር ይባላል፡፡
- አንድ ሽማግሌ በለበሰው ቲሸርት ላይ እንዲህ የምትል አንዲት ግሩም ዐረፍተ ነገር ተጽፋለች፡- ‹‹እኔ የስድሳ ዓመት ሽማግሌ አይደለሁም፣ የአርባ አራት ዓመታት የሕይወት ልምድ ያለኝ የአሥራ ስድስት ዓመት ወጣት እንጂ፡፡›› ይህ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ያሳያል፡፡
- እንዳለ ገነቦ እንዳለ