Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው

በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው

ቀን:

  • ብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚቴ በክልሎችም ሊቋቋም ነው

በቅርቡ ተቋቁሞ ወደ ሥራ የገባው የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ አካሄድኩት ባለው የሙስና ማጣራት ተግባር በተለያዩ ዓይነት ወንጀሎች የተጠረጠሩ የመንግሥት ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኮሚቴው ሰብሳቢና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህና የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኮሚቴውን ሥራዎች ክንውን አስመልክቶ ኅዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

መንግሥት ተግባራዊ ሊያደርጋቸው ለሚፈልጋቸው የኢኮኖሚና የፖለቲካ ለውጥ ዕርምጃዎች ሙስና ትልቅ እንቅፋት መሆኑን በመረዳት ተገቢውን ሕጋዊ የዕርምት ዕርምጃ ለመውሰድ የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን በመግለጽ ኮሚቴው ከሕዝብ የተገኙ ጥቆማዎችንና ቀደም ሲሉ የተሠሩ የጥናት ሥራዎችን መሠረት በማድረግ ሥራውን መጀመሩን ጌዲዮን (ዶ/ር) በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

የሕዝብን ጥቆማና ጥናትን መሠረት በማድረግ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የመንግሥት ኃላፊዎች መካከል የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴድሮስ በቃሉን አንዲሁም ስማቸው ያልተጠቀሱ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ውስጥ በመምርያ ደረጃ ኃላፊ የሆኑ ግለሰቦችን ጨምሮ  በርካታ የፍትሕና ፀጥታ የሥራ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

በጥናቱ በዋነኝነት የተለዩ የተባሉት የመሬትና የመንግሥት ቤቶች አስተዳደር የፀጥታ የፍትሕ ዘርፍ፣ የፋይናንስ ዘርፍ፣ የመንግሥት ገቢና ጉምሩክ ሥርዓት የአገልግሎት አሰጣጥ አስተዳደር፣ የመንግሥት ግዥና የመሳሰሉ ዘርፎች ናቸው፡፡

ኮሚቴው ሥራውን እንደጀመረ የቅድሚያ ቅድሚያና ትኩረት ያደረጋቸው ዘርፎች የፀጥታና የፍትሕ ዘርፍና ከመሬት አስተዳደር ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል፡፡

የሕዝብና የመንግሥት አደራ ወደ ጎን በመተው ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የአርሶ አደር ልጆች ያልሆኑ ግለሰቦችን የአርሶ አደር ልጆች በማስመሰል የልማት ተነሺ ያልሆኑ ሰዎችን የልማት ተነሽ በማስመሰልና በሕገወጥ መንገዶች የሐሰት ሰነዶችን በማዘጋጀት በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም በቦሌ፣ በንፋስ ስልክ፣ በአቃቂ፣ በለሚ ኩራና በየካ ክፍለ ከተሞች በርካታ የወንጀል ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ጌዲዮን (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡

በምርመራው 175,000 ካሬ ሜትር መሬትና ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የመዘበሩ እንዲሁም የመንግሥት ኮንዶሚኒየም ቤቶችን በሐሰተኛ ማስረጃ የወሰዱ የሥራ ኃላፊዎች፣ ደላሎችና የሕገወጥ ጥቅም ተካፋይ የሆኑ ግለሰቦች መለየታቸን አክለው ገልጸዋል፡፡

በተደረገው ምርመራ በወረራ የተወሰዱ መሬቶች የታገዱ መሆኑንና የተለዩ የወንጀል ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እየወሉ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራ እንደሚቀጥልና ሕዝቡ ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

በሌላ በኩል በፍትሕና በፀጥታ ዘርፍ ሥልጠናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም የዜጎችን ሰላምና የአገርን ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነታቸውን ተገን አድርገው በተለያየ ሕገወጥ መንገድ ከግለሰቦችና ከንግድ ድርጅቶች ገንዘብና ሀብት ለመውሰድ የተንቀሳቀሱ ተጠርጣሪዎች መለየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሀብታቸውን ሕጉ ባስቀመጠው ሥርዓት መሠረት ያላስመዘገቡ የመንግሥት ኃላፊዎችን ንብረትና በተለይም ቤት የማገድ ሥራ መጀመሩንና ይህን ሥራ በማጠናከር አስተማሪ የሆኑ ቅጣቶችንና የወንጀል ተጠያቂነትን ጨምሮ ንብረት እስከ መውረስ የሚደርስ የቅጣት ዕርምጃ በቀጣይ በስፋት እንደሚወሰድም አብራርተዋል፡፡

‹‹ሌብነት ነውርና ጥዩፍ የሆነ ወንጀል መሆኑን የሚያስገነዝቡ ተከታታይና አስቸጋሪ የዕርምት ዕርምጃዎች ይወሰዳሉ፤›› ተብሏል፡፡

ኮሚቴው ከተመሠረተ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ250 በላይ ጥቆማዎች  መድረሳቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ የፀረ ሙስና እንቅስቃሴ በቀጣይ በክልሎችም ተመሳሳይ አደረጃጀት በማቋቋም ሥራ እንደሚጀመር ተነግሯል፡፡ በመሆኑም ችግሩ ውስብስብ በመሆኑ የዘመቻ ሥራ ሳይሆን በተከታታይ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ መሰል ዕርምጃዎች እንደሚወሰድ የተናገሩት ጌዲዮን (ዶ/ር) ተጠርጣዎች ሀብት ማሸሽ እንዳይችሉና እንዲያዘዋውሩ በትኩረት ይሠራል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...