Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየጎደፈውን የኢትዮጵያ ገጽታ የሚያድስ የዲፕሎማሲ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

የጎደፈውን የኢትዮጵያ ገጽታ የሚያድስ የዲፕሎማሲ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ቀን:

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የጎደፈውን የኢትዮጵያ ገጽታ የሚያድስ የተጠናከረ የዲፕሎማሲ ሥራ መጀመሩን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ መለስ ዓለም (አምባሳደር) ዓርብ ኅዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት በፈተና ውስጥ ያለፈውን ዲፕሎማሲ የበለጠ በማጠናከር ከጥር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ሥራዎችን ለማናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ በመካከለኛ ደረጃ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና መጠናቀቁንና ከታኅሳስ 9 እስከ 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ወደ አዲስ አበባ ተጠርተው ሥልጠና እንደሚወስዱ፣ ባለፉት ዓመታት የነበሩትን የዲፕሎማሲ ፈተናዎች በተሻለ መንገድ ለማከናወን የታሰበ ትልም ስለመኖሩ አስረደተዋል፡፡

በዚህም ሊካሄድ በታሰበው ሥራ ከገጽታ ግንባታ አንፃር ከጦርነቱና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የነበሩትን ዲፕሎማሲዊ ችግሮችን ለማደስ፣ በሁሉም ሚሲዮኖች ትኩረት ያደረገ ሥራ እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ ‹‹ኢትዮጵያን ታድገዋል ቢባል ማጋነን አይሆንም፤›› ያሉት ቃል አቀባዩ፣  መንግሥትም የዜጎች ክብር እንዲጠበቅ እንደሚሠራና በተመሳሳይ ዜጎች ደግሞ በአገራቸው ጉዳይ አስተዋጽኦና ተሳትፎ እንዲኖራቸው ስለሚጠበቅ ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከጦርነቱ እየወጣች በመሆኑ በድኅረ ጦርነት ዓለም አቀፍ ፋይናንስ የማሰባሰብ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚከናወን፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን መገንባት፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ነበሩበት መመለስና እንዲቋቋሙ መሥራት ተገቢ የሆነ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚከናወን በመጠቆም፣ ይህን ተግባር ለማከናወን እንዲያግዝ በውጭ ያሉ ኤምባሲዎች እንደ ዋና ተግባራቸው አድርገው ይሠራሉ ብለዋል፡፡

ዲፕሎማሲው ተቀባይነት እንዲኖረው በባለቤትነትና በአሉታዊ ጎን የቆሙትን አገሮች የማለዘብ፣ ወዳጅ የማብዛትና ጠላት የመቀነስና የአገርን ጥቅም የማረጋገጥ ሥራ ይከናወናል ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሊካሄድ የታሰበው የአምባሳደሮች ስብሰባ የተለመደውን ዓይነት ዓመታዊ ስብሰባ ሳይሆን፣ አምባሳደሮችን አሁን ካለው ተጨባጭና ተለዋዋጭ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል የዲፕሎማሲ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...