Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአማራ ክልል በጦርነቱ የተመናመነውን የእንስሳት ሀብት ለመመለስ የሚያስችል ዕቅድ ማዘጋጀቱን ገለጸ

የአማራ ክልል በጦርነቱ የተመናመነውን የእንስሳት ሀብት ለመመለስ የሚያስችል ዕቅድ ማዘጋጀቱን ገለጸ

ቀን:

በሦስት ምዕራፍ በተደረገው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መጠነ ሰፊ ጉዳት የደረሰበት የአማራ ክልል፣ ጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች የተመናመነውን የእንስሳት ሀብት ለመመለስ የሚያስችል ዕቅድ ወደ ሥራ ማስገባቱ ተገለጸ፡፡

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ነጋ ይስማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እንስሳት በጦርነት ወቅት ከሰው ባላነሰ ከፍተኛ ሰለባ ይሆናሉ፡፡ በአማራ ክልልም የነበረው ጦርነት ምን ያህል የክልሉን የእንስሳት ሀብት ላይ ጉዳት አድርሷል? የሚለውን በገለልተኛ አካል ጥናት አስጠንቷል፡፡

የሰሜኑ ጦርነት ካደረሰው ሰብዓዊ ጉዳት በተጨማሪ በተለያዩ ምዕራፎች በመደረጉ፣ በእንስሳ ሀብት ላይ ውድመት ማድረሱን፣ ይህ ብቻም ሳይሆን እንስሳት በሌላ መንገድ በጦርነት ወቅት ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ በመሆናቸው፣ በዘርፉ ላይ የሚደርሰው ተፅዕኖ ተደራራቢ መሆኑን አቶ ነጋ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በክልሉ የነበረውን የእንስሳት ሀብት ወደነበረበትና ከዚያም በላይ ለመመለስ አዲስ ዕቅድ ማዘጋጀቱን የገለጸው የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት፣ ይህም የወደሙ የንብ ቀፎችን የመተካትና የሄዱ ሕብረ ንቦችን እንደገና የማባዛትና የመመለስ፣ የፈረሱና የተቃጠሉ የእንስሳት ጤና ተቋማትን የመገንባት እንዲሁም ከእንስሳት ሀብት ዝርያ ማሻሻል ጋር የወደሙ ተቋማትን እንደገና የመመለስ ሥራዎችን የሚያጠቃልል መሆኑን አስታውቋል፡፡

‹‹መልሰን የምናገግምበት፣ መልሰን የምንገነባበት ዕድል አለን፣ ብዙ ወድሟል፣ ብዙ ጠፍቷል፣ እንስሳት ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ በዚያው መንገድ፤›› በማለት የገለጹት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፣ የተዘጋጀው አዲስ ዕቅድ የሕዝቡን ሥነ ልቦና ሊጠግን በሚችል መንገድ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የአማራ ክልላዊ መንግሥት በመደበው በጀት በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች፣ የሀብት ማሰባሰብና የወደሙ መሠረታዊ አገልግሎት መስጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በራያ ቆቦ ወረዳ  ኅዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ብቻ በአማራ ክልል በነበረው ጦርነት ከ292 ቢሊዮን ብር በላይ ውድመት መድረሱ በጥናት መረጋጋጡ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህንን መልሶ ለመገንባት ክልሉ በተያዘው የበጀት ዓመት ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ለማሰባሳብ ማቀዱ ታውቋል፡፡

እስካሁን የክልሉ መንግሥት ከራሱ በጀት በመደበው አንድ ቢሊዮን ብር ጉዳት በደረሰባቸው ስምንት ዞኖች ሦስት ሺሕ ቤቶች፣ 21 ትምህርት ቤቶች፣ 10 ጤና ጣቢያዎች፣ 31 የንፁህ መጠጥ ውኃ እንዲሁም የአንድ ሆስፒታል የመልሶ ግንባታ ሥራ እንደሚያካሂድ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...