Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአፍሪካ ምርቶች በአንድ የጥራት ደረጃ ሥር እንዲያልፉ እንቅስቃሴ ተጀመረ

የአፍሪካ ምርቶች በአንድ የጥራት ደረጃ ሥር እንዲያልፉ እንቅስቃሴ ተጀመረ

ቀን:

አገሮች ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ እንዲያቀርቡ ያስችላል የተባለው በአፍሪካ የሚመረቱ ምርቶችን በአንድ የጥራት ደረጃ ሥር የማሳለፍ እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በኢንስቲትዩቱ አዘጋጅነት ከኅዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚካሄደው 67ኛው የአፍሪካ ደረጃዎች ምክር ቤት ጉባዔ ሲከፈት የተገኙት የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር መሠረት በቀለ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ የአገር ውስጥ ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያ እንዲውል ተፈላጊ እንዲሆኑ የአፍሪካ ደረጃዎችን ማሟላት ይገባል፡፡

  ጉባዔው በዋናነት በአፍሪካ አገሮች የሚመረቱ ምርቶችን በአንድ የጥራት ደረጃ ሥር እንዲያልፉ የማድረግ ትልም ያነገበ መሆኑንና ይህም ነፃ የንግድ ቀጣናን ለማሳለጥ እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያን ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ፣ መጀመርያ የአፍሪካ ደረጃዎችን ማሟላት እንደሚገባ የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ ምርቶችን የማስማማት ሥራ እንደሚሠራም ተናግረዋል፡፡

በጉባዔው ምርቶችን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለማውጣት የሚያስችሉት የአፍሪካ ደረጃዎች ላይ እንደሚመክሩበት ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ የደረጃዎች ድርጅት ፕሬዚዳንት አሌክስ ዶዶ (ፕሮፌሰር) ‹‹ደረጃ ከሌለ ንግድ አይኖርም፡፡ ንግድ ከሌለ ኢኮኖሚ አይኖርም፡፡ የምርቶች ደረጃዎች ማውጣትና ማዘጋጀት ለንግድ፣ ለኢኮኖሚና ማኅበራዊ ዕድገት ቁልፍ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የጉባዔው ዓላማም በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የሚመረቱ ምርቶችን ደረጃዎች አንድ የማድረግ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡ ይህም በዓለም ገበያ ለመወዳደር የአፍሪካ ደረጃ አንድ መሆን እንዳለበት፣ የጉባዔውም ዓላማ ምርቶቹን አንድ ደረጃ እንዲኖራቸው ማድረግ መሆኑን አሌክስ (ፕሮፌሰር) አስረድተዋል፡፡

መሠረት (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች የአገር ውስጥ ደረጃ ሊያሟሉ እንደሚችሉ ሆኖም፣ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ገበያ ውስጥ ለመግባት የአፍሪካ ደረጃዎችን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡

የአፍሪካ ደረጃዎች ድርጅት 43 አባል አገሮች ያሉት ሲሆን ከ12 የምክር ቤት አባላት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...