Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

በሆንኩኝ አቧራ

ትኩስ ፅሁፎች

‹‹ዓይቶ ዝም ሰምቶ ዝም፣

ከሆድ ያለ አይነቅዝም፡፡››

ይላል እያረረ፣

ውስጥ ውስጡን ሲብሰው፡፡

እኔ አፍቃሪ ሆኜ አንቺ ተፈቃሪ፣

በትነሽ ልትዘሪኝ፣

አጭደሽ ልትከምሪኝ፣

ዘርጥጠሽ ልትወቂኝ፣

ሁሌም ስትሞክሪ፣

በጣለብኝ ዕዳ ሌላ ምን እላለሁ፣

ሁሉን ስታደርጊኝ ቻል አደርገዋለሁ

ይልቅ ከዚህ ሁሉ፣

ምነው ባደረግሽኝ ብናኙን አቧራ፣

ነፋስ ተሸክሞኝ ካይንሽ እንድገባ፣

ባይንሽ እንድሞላ፡፡

  • መዝገበ አየለ ገላጋይ ‹‹ዶፍ አዘል ደመና›› (2013)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች