ስታሊን በተረቡና ቀልዶቹ የሚታወቀውን ሬዴክ አስጠርቶ፣ ‹‹ስለኔ ቀልዶችን እንደምታወራ አውቃለሁ፡፡ ይኼ አግባብነት የሌለው የብልግና ሥራ ነው›› አለው፡፡
‹‹ለምን?››
‹‹ታላቅ መሪ፣ መምህር፣ እና ሕዝብ ወዳድ ነኛ!››
‹‹ጓድ፣ ይህን ቀልድ ለማንም አልነገርኩም፡፡››
ቀልደኛው ራቢኖቪች ‹‹ሌኒን ቢሞትም፣ ሥራው ሕያው እንደሆነ ይቀጥላል!›› የሚለውን መፈክር በሰማ ጊዜ ‹‹የተገላቢጦሹ ቢሆን ይሻል ነበር›› አለ፡፡