Tuesday, September 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ፍትሐዊ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል የተባለው የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ እየተካሄደ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከኢንተርኔት ግንኙነት ውጪ የሆኑ ሕዝቦችን በኢንተርኔት ማገናኘትና ሰብዓዊ መብትን መጠበቅ፣ ኢንተርኔትን በአግባቡ ማስተዳደርና የግል ዳታ ጥበቃ፣ ደኅንነትንና ተጠያቂነትን ማስፈን፣ ወቅታዊ ቴክኖሎጂዎች የሆኑትን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence)፣ የኢንተርኔት መከፋፈልን (Fragmentation) ማስቀረት በሚሉ አምስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርግና ፍትሐዊ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል የተባለው 17ኛው የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡

ሰኞ ኅዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በተጀመረው ጉባዔ ላይ ከ3,000 በላይ የተለያዩ አገሮች ተወካዮች የሚሳተፉበት ሲሆን፣ ዲጂታል ኢኮኖሚ ልማትንና ተወዳዳሪነትን በቀጣይነት የሚያረጋግጡ፣ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎች፣ ሕጎችንና ፕሮግራሞችን በመቅረፅ የአገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ መገንባትና የዜጎች በዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት ውስጥ ፍትሓዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የጉባዔው ዋና ዓላማ እንደሆነ ተነግሯል።

ጉባዔው ‹‹የማይበገር ኢንተርኔት ለዘላቂና እኩል የጋራ ተስፋ›› በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ የ17ኛው ዓለም አቀፍ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባዔ ሴክሬታሪያት ሰብሳቢና በኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የግል ዘርፍ ቴክኖሎጂ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሥዩም መንገሻ ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባዔን ኢትዮጵያ ማዘጋጀቷ ከሚያስገኘው የፖለቲካዊ፣ የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጥቅሞች ባሻገር፣ ዲፕሎማሲያዊ ትሩፋቱ የጎላ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ የኢትዮጵያን ሰላምና ብልፅግና የማይፈልጉ አንዳንድ አገሮች፣ አገሪቱ ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ ኮንፍረንሶችንና ስብሰባዎች፣ በአቅም ማነስና በሰላም ዕጦት ማዘጋጀት እንደማትችል በመግለጽ የአገሪቱን ስም በማጠልሸት ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዳትሆን በርካታ የዲፕሎማሲ አሻጥሮችን የሚሠሩ እንዳሉ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ 17ኛውን ዓለም አቀፍ ጉባዔ በማዘጋጀቷ አንዳንድ የምዕራባውያን ሚዲያዎች እንደሚዘግቡት ሳይሆን፣ አስተማማኝ ሰላም ያላት እንደሆነች ሁነቱን በዓለም ዙሪያ ለሚዘግቡት መገናኛ ብዙኃንና ከተለያየ አገሮች የሚመጡ እንግዶች ለማሳየት መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥርም አክለዋል።

ጉባዔውን የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት በኮቪድና በሌሎች ሰው ሠራሽ ችግሮች በተፈተነችበት ወቅት ሥራን በበይነ መረብ ማካሄድ መቻሏን፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በትኩረት እየሠራች መሆኑነ፣ ያላትን የሕዝብ ቁጥር ያማከለ የኢንተርኔት ተደራሽነት ለማሳደግ በሥራቸው ሥራ ብዙ ለውጦች ማምጣቷን፣ የኢንተርኔት ሽፋን በፈረንጆቹ 2017 ከነበረው 19 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች በ2022 ወደ 30 ሚሊዮን ማደጉንና ሌሎች በርካታ ሥራዎችን መሥራቷን አብራርተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች