የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015 ዓም የባንኩ ካፒታል 55 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ያቀረበውን ሃሳብ ጠቅላላ ጉባኤው ተቀብሎ አጸደቀ።
ባንኩ ባሁኑ ጊዜ 12 ቢሊይን ብር የፈረመና 10.3ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ያለው ሲሆን፣ዛሬ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ 43 ቢሊዮን ብር በመጨመር ካፒታሉ ወደ 55 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል ውሳኔ አሳልፏል።ከተጨማሪው 43 ቢሊዮን ብር 38 ቢሊዮን ብር ግምት ያላቸውን አክሲዮኖች ነባር ባለድርሻዎች ይገዙታል ተብሏል።
ሁለት ቢሊዮን ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች ደግሞ፣ለባንኩ ሠራተኞች እንዲሸጥ ጠቅላላ ጉባኤው ወስኗል።ጉባኤው፣ ለባንኩ ነባር ደንበኞችና የሥራ አጋር ኩባንያዎች የሦስት ቢሊዮን ድርሻ በ50 በመቶ ፕሪሚየም እንዲሸጥላቸው የቀረበውን ሃሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።