Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየ ሳ ም ን ቱ ገ ጠ መ ኝ

የ ሳ ም ን ቱ ገ ጠ መ ኝ

ቀን:

በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ሳስብ የሕወሓት ሰዎች ነገር ከፊቴ ድቅን ይልብኛል፡፡ ከዛሬ ሃያ ዓመት በፊት በመጀመሪያው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን አንድ መደበኛ ስብሰባ ዕለት፣ አንድ የአፋር ሕዝብ ተወካይ የሆኑ የምክር ቤት አባል ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ያቀረቡት አስገራሚ ጥያቄ ለዛሬው ጽሑፌ መነሻ ሆኖኛል፡፡ የአፋሩ ተወካይ በወቅቱ በክልላቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽፋን በጣም አነስተኛ መሆኑን፣ ነገር ግን በክልላቸው ውስጥ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር የአፋር ሕዝብን ተሻግሮ ወደ ሌላ ክልል (ትግራይ) ኃይል ተሸክሞ እንደሚሄድ በማስታወቅ ጉዳዩን በሚያስገርም ተረት አቀረቡት፡፡

‹‹በአፋር አንድ ተረት አለ፡፡ አንድ ዓይነ ሥውርና ዓይኑ የሚያይ ሰው ገንፎ በቅቤ ተሠርቶ ቀረበላቸው፡፡ ዓይኑ የሚያየው ሰው ቅቤውን በራሱ በኩል አድርጎ ደረቁን ገንፎ በዓይነ ሥውሩ በኩል አደረገ፡፡ ዓይናማው ገንፎውን በቅቤ ሲበላ ዓይነ ሥውሩ ግን እየበላ አልነበረም፡፡ ዓይናማው ‹ለምን አትበላም› ሲለው፣ ‹ለአፍንጫዬ የደረሰው ቅቤ ለአፌ ካልደረሰው ደረቁን ለምን እበላለሁ› አለው፡፡ የአፋር ሕዝብም እንደ ዓይነ ሥውሩ ነው የሆነው…›› ሲሉ መለስ አበዱ፡፡ እኔ በዚያን ቀን ምሽት የተላለፈውን የፓርላማ ውሎ በቴሌቪዥን አይቼው ስለነበር፣ የአቶ መለስ ንዴት በጉልህ ነበር የሚታየው፡፡

የአፋሩ ተወካይ በተረት አሽሞንሙነው ያቀረቡት ቁጭት የተሞላበት ቅሬታ በጣም ሸንቋጭ፣ ነገር ግን ያፈጠጠውን አድሎአዊነት በሚገባ የሚያሳይ ስለነበር አቶ መለስ ያልጠበቁት ነበር ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ አቶ መለስ በምክር ቤት አባላት የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ገረፍ ገረፍ አድርገው ከመለሱ በኋላ፣ ለአፋሩ ተወካይ አናዳጅ ስሞታ የሰጡት የመልስ ጊዜ ከአንድ ሰዓት ይበልጥ ነበረ፡፡ አቶ መለስ ገንፎ ለመብላት መሬት አለስልሶ ከማዘጋጀት እስከ ገብስ ማምረትና ገንፎውን ማዘጋጀት ድረስ ያለውን ሒደት ሲገልጹ፣ በንዴት ጠረጴዛውን እየደበደቡና ረጅም ትንታኔ እያቀረቡ ነበር፡፡

ቅቤውን ለማግኘት ደግሞ የሰጡት ዝርዝር ከአርብቶ አደር ማኅበረሰብ ለወጡት የአፋር ተወካይ አስገራሚ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የአፋሩ ተወካይ በመገረምና ወይ ሥልጣን እንዲህ ያናግራል ለካ የሚል ስሜት ይነበብባቸው እንደነበር ለመገንዘብ መቻሌን አስታውሳለሁ፡፡ አቶ መለስ ገንፎም ቅቤም ለማግኘት ወገብ እስከሚጎብጥ ቀንና ሌሊት መሥራት ያስፈልጋል ሲሉ፣ እኔ ደግሞ ይህ ሁሉ ሀተታ በአድሎአዊነት ወደ ክልላቸው ያስዘረጉትን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማድበስበስ እንደነበረ በቀላሉ ስለገባኝ እየሳቅኩ ነበርኩ፡፡ የአፋሩ ተወካይ ግን ካሜራው ድንገት ብልጭ ሲያደርጋቸው ‹እሱን እንኳ ተወው› የሚሉ ይመስሉ እንደነበር ገጽታቸው ከመጠን በላይ ይናገር ነበር፡፡

ምንም እንኳ አቶ መለስና ሕወሓት የተባለው ድርጅታቸው አድሎአዊ ሥርዓታቸው ገና ከጅምሩ ቢነቃበትም፣ እሳቸው ግን አልፈው ተርፈው ሌላ ክስ አመጡ፡፡ አፋር የሚሰጠውን በጀት በአግባቡ ባለመጠቀሙና የማንም መጫወቻ መሆኑን ለመግለጽ፣ ‹‹የአፋር በጀትና ቀዳዳ ገረወይና አንድ ነው…›› ብለው አረፉ፡፡ አንድን ስህተት ለማረም ሌላ ስህተት መፈጸማቸውን ግን በወቅቱ አልተረዱትም፡፡ እሳቸው እኮ ነበሩ ከዓመታት በኋላ የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኃላፊ የነበሩትን አቶ ለማ አርጋው፣ ‹‹ክልሎች በጀታቸውን ቢያቃጥሉት ምን ያገባችኋል…›› ብለው የነበሩት፡፡ በአፋሩ ተወካይ የተበሳጩት አቶ መለስ ሥርዓታቸው ምን ዓይነት ዝቅጠት ውስጥ እንደ ገባ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡

እዚህ ላይ የማልረሳው በዚያን ጊዜ ሰሜን ጎንደር ውስጥ ነው አሉ፡፡ ሁለት አርሶ አደሮች እርሻ ውለው ሲመለሱ መሽቶባቸው ነበርና ከፊታቸው ኩራዝ ወይም ማሾ የሚያበሩ ሰዎች ዘንድ ይደርሳሉ፡፡ አርሶ አደሮቹ እንደ ደረሱ ሦስት ሆነው ትልቅ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሥር የተቀመጡትን ሰዎች፣ ‹‹ምነው ምን ሆናችሁ ነው…›› ሲሏቸው፣ ከተቀመጡት አንደኛው እየሳቀ፣ ‹‹ትግሬን እራት እያበላን ነው…›› ብሎ ይመልሳል፡፡ ለካ በዚያን ጊዜ የኤሌክትሪክ መስመሩ ጥቃት ሊፈጸምበት ስለሚችል በገበሬ ማኅበር ለጥበቃ ታዘው የወጡ ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገሩ ቀልድ ይሁን የምር ባላውቅም፣ ሕወሓት የመሠረተው አድሎአዊ ሥርዓት አግላይነት አንዱ ማሳያ ነበር፡፡ የአፋሩ ተወካይ ስሞታ ሲታከልበት ደግሞ እውነት ነበር ለማለት ያስችላል፡፡

ሕወሓት መራሹ ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ምድር የሠራው ግፍ ከዚህም በላይ ተሻግሮ የብዙዎችን ሕይወት የነጠቀ፣ ያሰቃየ፣ ያሰደደ፣ ለእስርና ለእንግልት የዳረገ እንደነበር ማንም የሚያውቀው ነው፡፡ ሕወሓት ከማዕከል በሕዝብ ግፊት ተባሮ ከግፉና ከዘረፈው ሀብት ጋር ቢሸኝም፣ ክልሉ ገብቶ ኢትዮጵያን በእጅ አዙር ሲያተራምስና ሊያፈርስ ሲያደባ ቆየ፡፡ ይህም አልበቃው ብሎ ጦርነት አስነስቶ ያጣውን ሥልጣን በእጅ አዙር የሚያገኝበት እሳት ቢጭርም፣ ራሱ ተቃጥሎ እንዳይሆኑ ሆኖ እየመረረውም ቢሆን ለሰላም ድርድር ሮጦ ፕሪቶሪያና ናይሮቢ ድረስ መሄዱ ይታወቃል፡፡

ይህ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያስደስት ጉዳይ ሆኖ ሳለ የሕወሓት አጋፋሪዎች ዛሬም አለን እያሉ ነው፡፡ ሕወሓት የሰላም ድርድሩን ለጊዜ መግዣ እየተጠቀመበት እንደሆነ በተዘዋዋሪም ቢሆን እየነገሩን ነው፡፡ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከጥምር ጦሩ ጋር እንዳይሆኑ አድርጎ ቢደቁሰውም፣ መራራውን ሽንፈት ባለመቀበል የኤርትራ ሠራዊት ትግራይ ውስጥ እየገደለና እየዘረፈ ነው በማለት አዲስ ትርክት ያሰማል፡፡ ሁሌም በውሸት ትርክት ዓለምን ማወናበድ የተካነበት የሽፍትነት ተግባሩ ስለሆነ አሁንም ገፍቶበት በመቀጠል፣ የሰላም ሒደቱን ፈተና ውስጥ ሊከተው እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ‹‹እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም›› እንደሚባለው መንግሥት ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ፣ ያጣነውን ሰላምና ዕፎይታ ያረጋግጥልን፡፡ በሕወሓት ውሸት አገራችንና ሕዝባችን አይበጥበጡ፡፡

 (ሸረፋ ያሲን፣ ከጎተራ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...