Thursday, September 28, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  • ሄሎ… ማን ልበል?
  • ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር?
  • ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል?
  • የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡ 
  • አቤት?
  • ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡
  • ኦ… ገባኝ… ገባኝ… 
  • ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል?
  • ትይዩ ስትል መጠሪያ ስምህ መስሎኝ ማነው ብዬ እኮ ነው ትንሽ ግር ያለኝ።
  • ገብቶኛል… ያው በስም አያውቁኝም ብዬ ነው…
  • አሁንማ አወቅኩህ… አቻዬ ነህ…
  • ኪኪኪ… ያው የደወልኩት አንድም አድናቆቴን ለመግለጽ፣ አንድም ያልገቡኝ ጉዳዮችን እንዲያብራሩልኝ ነው።
  • መልካም፣ ደስ ይለኛል፡፡
  • በመጀመሪያ ሙሰኞችን ለመመንጠር ሰሞኑን ያሳለፋችሁትን ውሳኔ ፓርቲያችን እንደሚያደንቀውና በእጅጉ እንደሚደግፈው ልገልጽልዎት እወዳለሁ። 
  • አመሠግናለሁ፣ ያው እንደምታውቀው ትግሉ ለመንግሥት ብቻ የሚተው ሳይሆን የጋራ ኃላፊነታችን መሆን አለበት። 
  • እስማማለሁ ክቡር ሚኒስትር፣ ነገር ግን አንዳንድ ግልጽ ያልሆኑልኝ ጉዳዮች አሉ። 
  • ጥሩ፣ ምንድነው ግልጽ ያልሆነልህ?
  • ክቡር ሚኒስትር ሙስናን ለመዋጋትም ሆነ በሙሰኞች ላይ ዕርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት የተሰጣቸው ተቋማት እያሉ፣ ለምን ጉዳዩን በኮሚቴ ለመሥራት እንደፈለጋችሁ ግልጽ አልሆነልኝም፡፡
  • ልክ ነው፣ ከተቋቋመ ረዥም ዓመታትን ያስቆጠረ የፀረ ሙስና ኮሚሽን አለን፣ በተጨማሪም እንዲህ ዓይነት ወንጀሎችን ተከታትሎ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን የዓቃቤ ሕግ ክፍል በፍትሕ ሚኒስቴር ውስጥ አለ። 
  • እኮ ለዚህ ነው እኔም በኮሚቴ መሥራት ለምን ተፈለገ የሚል ጥያቄ የጫረብኝ። 
  • ጥያቄው መናሳቱ ተገቢ ነው፣ ግን ኮሚቴው የተቋቋመው ድጋፍ ለማድረግ እንጂ የሕግ ማስከበር ሥራው ሕጋዊ ሥልጣን በተሰጣቸው ተቋማት ነው።
  • ኮሚቴው የምን ድጋፍ ነው የሚሰጠው? 
  • እንምታውቀው የሙስና ወንጀል በረቀቀ መንገድ ነው የሚፈጸመው፣ የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎችና የፋይናንስ ተቋማት የመሳሰሉት ይሳተፉበታል። 
  • አዎ፣ ልክ ነው።
  • ስለዚህ ኮሚቴው በየዘርፉ ሙያዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ታስቦ ነው የተቋቋመው፣ የኮሚቴ አባላቱን ስብጥርን ብትመለከትም ይህንኑ ነው የሚጠቁምህ። 
  • አሃ… አሁን ግልጽ ሆኖልኛል፣ ቢሆንም ግን ኮሚቴው ሌላ ተልዕኮ እንደሌለው የምንከታተለው ይሆናል። 
  • የምን ተልዕኮ? 
  • በሕግ መጠየቅ ያለባቸውን ሙሰኞችን የማመጣጠን ተልዕኮ፡፡
  • የምን ምጥጥን?
  • የብሔር፡፡
  • አይ… እንዲያ እንኳ አይደለም፣ ግን…
  • ግን ምን ክቡር ሚኒስትር?
  • እንደምታውቀው ሙሰኞች ልትነካቸው መሆኑን ሲያውቁ ብሔራቸውን መሸሸጊያ ያደርጋሉ።
  • ሊሆን ይችላል።
  • ሊሆን ይችላል ሳይሆን እንደዚያ ነው የሚያደርጉት።
  • ስለዚህ?
  • አንድን ሕገወጥ ድርጊት እናስቆማለን ብለን የባሰ ችግር እንዳንፈጥር ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ለማለት ነው። 
  • በጥንቃቄ መፈጸሙን ማነው የሚያረጋግጠው?
  • ኮሚቴው!

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ገብተው ገና አረፍ እንዳሉ ባለቤታቸው በአግራሞት እየታዘቧቸው መሆኑን አስተዋለው ምን ተፈጠረ ሲሉ ጠየቁ]

  • ምነው? ምን ተፈጠረ?
  • በቴሌቪዥኑ የሰማሁት አንድ ዜና አስደንግጦኝ ነው፡፡ 
  • በመንግሥት ቴሌቪዥን ነው?
  • አዎ።
  • በመንግሥት ቴሌቪዥን የሚያስደነግጥ ዜና? 
  • ለማስደንገጥ ብለው ላይሆን ይችላል ግን… 
  • ግን ምን?
  • እኔን አስደንግጦኛል፣ እንዲሁም አስገርሞኛል…
  • ዜናው ሰለምን ጉዳይ ነው? 
  • የእናንተው ጉድ ነው፣ እናንተ የማታመጡብን ነገር ምን አለ?
  • ለምን በግልጽ አትነግሪኝም?
  • ወጣቶችን ወደ ብሔራዊ ውትድር ልታስገቡ ስለመሆኑ ነዋ፡፡
  • ታዲያ ምኑ ነው የሚያስደነግጠው?
  • እንዴት አያስደነግጥም? በደርግ ዘመን በነበረው ብሔራዊ ውትድርና ስንት ቤተሰብ እንደተንገላታ ዘንግተኸው ነው?
  • ይኼኛው እኮ ለየት ያለ ነው። 
  • ምኑ ነው የሚለየው?
  • አንደኛ ስያሜው የተለየ ነው። 
  • ስያሜው ምንድነው ታዲያ? 
  • ብሔራዊ አገልግሎት ነው። 
  • ሁለተኛስ? 
  • ሁለተኛ በዓላማው ይለያል፣ ሦስተኛ…
  • እሺ ሦስተኛስ?
  • ሦስተኛ አስገዳጅ አይደለም። 
  • እሺ እኔ በተራዬ ልጠይቅህ?
  • ስያሜው ብሔራዊ አገልግሎት ነው ስትል ምን ማለትህ ነው? ለምን አገልግሎት ነው የሚመለመሉት?
  • እሱማ ለውትድርና አገልግሎት ነው።
  • ታዲያ ምኑ ነው የሚለየው?
  • የውትድርና አገልግሎት ቢሆንም ለውጊያ ተፈልገው አይደለም። 
  • እሱንማ ዛሬ አትገልጹትም። 
  • እንዴት? እና መቼ ነው የምንገልጸው?
  • ጦርነት ሲመጣ ነዋ፡፡
  • እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ መጠራጠር አይለቅሽም፡፡
  • እሱን ተወውና ጥያቄዬን መልስ፡፡
  • መቼ አልመልስም አልኩኝ? ጠይቂኝ?
  • ዓላማው የተለየ ነው ብለሃል።
  • አዎ፣ ዓላማው የተለየ ነው።
  • በምንድነው የሚለየው?
  • ዓላማው ወጣቶችን ማነፅ ነው፣ አገራቸውን እንዲወዱ ማድረግ፣ አገራቸውን እንዲያውቁ ማድረግና ጥሩ ሥነ ምግባር የተለባሱ ዜጎችን ማፍራት ነው። 
  • እሱ እንኳ ጥሩ ነገር ነው ግን…
  • ግን ምን? 
  • በውትድርና ካልሆነ በሌላ መንገድ ማነፅ አይቻልም? 
  • ይቻላል ነገር ግን ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች የሚያሳዩት በውትድርና ቤት ሲሆን በተሻለ ፍጥነት ጥሩ ዲሲፕሊን ያለው አገሩን የሚወድ ትውልድ መቅረፅ እንደሚቻል ነው።
  • በተሻለ ፍጥነት ስትል በምን ያህል ጊዜ ነው? 
  • እኛ ያሰብነው የሁለት ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ነው። 
  • ሁለት ዓመት? 
  • አዎ፣ ሁለተኛ ደረጃ የጨረሱ ወይም ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቁ ወጣቶች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ብሔራዊ አግልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል። 
  • ሁለት ዓመት በጣም አልበዛም? የቀለም ትምህርቱን አይዘነጉትም? 
  • አይዘነጉትም፣ እንዲያውም የበለጠ ያዳብሩታል። 
  • ወይ ጉድ፡፡ 
  • ለምን ወይ ጉድ?
  • አንድ ጥሩ ነገር ያለው አስገዳጅ አለመሆኑ ብቻ ነው፣ አስገዳጅ አይደለም ብለሃል አይደል? 
  • አዎ፣ አስገዳጅ አይደለም፣ ግን…
  • ግን ካልክማ አስገዳጅ ነው ማለት ነው።
  • አይ አስገዳጅ አይደለም፡፡ 
  • ታዲያ ለምን ግን አልክ? ምን ልትል ነበር?
  • ግን ትምህርቱን የጨረሰ ወጣት ብሔራዊ አገልግሎት ወስዶ አገሩን ካላወቀ በመንግሥት ተቋም ውስጥ ሥራ አይቀጠርም፡፡ 
  • ስለዚህ አስገዳጅ አይደለም? 
  • አስገዳጅ አይደለም! 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...

ማን በማን ላይ ተስፋ ይኑረው?

በአንድነት ኃይሉ ችግሮቻችንን ለይተን ካወቅን መፍትሔውንና ተስፋ የምናደርግበትን ማወቅ እንችላለን፡፡...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሁለት ሳምንት ያክል የፓርቲ ስብሰባ ላይ ቆይተው አመሻሹ ላይ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ባለቤታቸው በአግራሞት ተቀብለው ስለቆይታቸው ይጠይቋቸው ጀመር]

እኔ እምልክ...? ውይ... ውይ... በመጀመሪያ እንኳን በሰላም መጣህ፡፡ እሺ ...ምን ልትጠይቂኝ ነበር? ይህን ያህል ጊዜ የቆያችሁት ለስብሰባ ነው? ስብሰባ ብቻ አይደለም። ከስብሰባ ውጪ ምን ነበር? በተለያዩ መሪ ሐሳቦች የተዘጋጁ ሥልጠናዎችን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን የፓርቲያቸውን የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ አጠናቀው ወደ ቢሯቸው ሲመለሱ ቢሯቸው ውስጥ አማካሪያቸው አንድ ጽሑፍ በተመስጦ እያነበበ አገኙት]

ምንድነው እንደዚህ መስጦ የያዘህ ጉዳይ? መጡ እንዴ ክቡር ሚኒስትር፣ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያወጣውን መግለጫ እያነበብኩ ነው፡፡ ግን እኮ ፊትህ ላይ የመገረም ስሜት ይነበባል፡፡ አዎ፣ መግለጫው ላይ...

[ክቡር ሚኒስትሩ እየጠራ ያለውን ሞባይል ስልካቸውን ተመለከቱ፣ የህዳሴ ግድቡ ተደራዳሪ መሆናቸውን ሲያውቁ ስልኩን አነሱት]

ሃሎ... ጤና ይስልጥኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስልጥልኝ ክቡር ተደራዳሪ... የጥረትዎን ፍሬ በማየትዎ እንኳን ደስ አለዎት፡፡ እንኳን አብሮ ደስ አለን፣ ምን ልታዘዝ ታዲያ? የውኃ ሙሌቱንና አጠቃላይ የግድቡን የግንባታ ሁኔታ...